March 6, 2024 – Konjit Sitotaw

ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ስለ ወቅታዊው የፋኖ ትግል ጠንከር ያለ መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ አጋርተዋል ይመልከቱት
ታላቁ ስእል ላይ ማተኮር ነው እሱም : የፋኖ አንድነትና : የፋኖ ተናቦ መስራት ነው:: ይህ የእስክንድር ራእይ ነው::
ይህንንም የጀመረው ያስጀመረው: እዚህ ያደረሰው እስክንድርና የሚመራው ግንባሩ ነው::
አሁን ከገባንበት አዲስ ምእራፍ ተነስተን ወደ ዋናው ግባችን ለመድረስ እስክንድርና ዘመነ እንዲሁም በየክፍለሀገሩ ያሉ የእዝና የፋኖ እዛዦች አብረው ተናበው እንዲስሩ ማበረታትና ማገዝ እንጂ: አሁን ባለቀ ስአት እዚህ ተቀምጠን እነሱን የሚከፋፍል ንግግር : መግለጫ : ወሬ መንዛት ከአቢይ የበለጠ ታላቅ ጠላትነት ነው::
የዛሬ ስራችን ሀላፊነታችን: ሜዳ ያለውን ከልጅነት እስከእውቀት: አንድም ቀን ከአገሩ ከህዝቡ ጥቅም ውጭ ስርቶ የማያውቀውን እስክንድርን መኮነን ማኮሰስ : በህሊናም በባህልም በእምነትም በአገር ወዳድነት ሚዛንም ያስጠይቃል:: ስአቱ ጊዜው አይደለም:::
እዚህ ድረስ ከመጣን በሁዋላ መሪዎቻችንን ማንኳሰስ: ግልፅ ጠላትነት ነው:: ቅሬታችን ክሳችን እውነት ነው ብላችሁ ካስባችሁ ለምን አራት ኪሎ ከገባን በሁዋላ እንጠያየቅም? አላማው ሌላ ነዋ !! ይህንን የማይረዳ ማንም አዋቂ አእምሮ ሊኖር አይችልም::
በተንኮል የተመረዘ ወይም የታመመ አእምሮ ካልሆነ:: የአማራን ፋኖ የሚያቆመው ምንም ሀይል በአለም ውስጥ የለም:: መሪዎችን ማጥላላት እንቅፋት እንጂ ግድግዳ አይደለም:: የአራት ኪሎ መንገድ ግድግዳ ፈርሷል::: ወደፊት እንጂ ወደኋዋላ የለም