March 6, 2024 – Konjit Sitotaw 

“የማሳሳቻና የማደናገሪያ መረጃ በማውጣት የሚቆም ትግል የለም” የአማራ ፋኖ በጎጃም የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ማርሸት ፀሐው!

አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ፋኖ የደረሰበትን ሽንፈት ለማወራረድ አማራ ክልልን በከባድ መሳሪያ  እየደበደበ መሠረተ ልማቶችን አውድሟል። ንፁኃንን ጨፍ*ጭፏል!

በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እንደ እባብ እየተቀጠቀጠ ያለው ኦህዴድ መራሹ የብልፅግና ስርዓት በጢስ አባይ አካባቢ “የፋኖ ታጣቂዎች አሉ” በማለት በከባድ መሳሪያ ሲደበድብ ሰንብቷል። ስለሆነም ብዙ መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፤ ንፁኃንን ጨፍ*ጭፏል። በዚህም ምክንያት መነሻውን ጢስ አባይ ያደረገውን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሳብስቴሽን አውድሞታል።

በውሸት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ነጭ የውሸት መረጃዎችን እያሰራጨ ይገኛል። በተለይም የአገዛዙ አዳሪ የሆነው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ከትላንት እኩለ ቀን ጀምሮ ለተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል፤ ምክንያቱ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር በጦር መሳሪያ እንደተመታ ካሳወቀ በኋላ  የኃይል ማስተላለፊያው በፋኖ ታጣቂዎች ነው የተመታው ሲል የተገላበጠ የውሸት መረጃውን አሳውቋል።

በትላንትናው ዕለት አብዛኛው የሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የኤሌክትሪክ ኃይል እንደተቋረጠበት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስታወቁን አዲስ ማለዳ ዘግባ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ እውነተኛ መረጃው ግን ተቋሙ ከባህር ዳር – በደብረታቦር – ንፋስ መውጫ – ጋሸና – አላማጣ የተዘረጋው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በብልፅግና ሰራዊት በከባድ መሳሪያ በመደብደቡ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

ማረጋገጥ የምንፈልገው ግን የአማራ ፋኖ ለመብራት ኃይል ሰራተኞች ልዩ ጥበቃ የሚያደርግ ይሆናል!

ፋሽስታዊው ፀረ-ህዝብ የአብይ አህመድ አገዛዝ በትግራይ ህዝብ ላይ እንዳደረገው፣ በአማራ ህዝብ ላይ የመብራት መስመሮችን ሆን ብሎ መቁረጡ ታውቋል። እራሱ ያቋረጠውን መስመርም ቀድሞ በፋኖ ለማላከክ በማሰብ በውድቅት ሌሊት መግለጫ ሰጥቷል።

ይህ ድርጊት በጦርነት ማንበርከክ ያልቻለውን የአማራን ህዝብ በተለያየ መልኩ ጫና ለማሳደር መሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን ህዝባችን የያዘው የመኖርና ያለመኖር ትግል በመሆኑ በመብራት መጥፋት ምክንያት ትግሉን አቋርጦ፣ እጁንና እግሩን አጣጥፎ ለዳግም የዘር ማጥፋት ይሁንታውን ይሰጣል የሚለው እሳቤ ፍፁም ፉርሽ ነው። በዚህ እርማችሁ አውጡ!

ፋኖ የመብራት መስመር መቁረጥ ካለበት፣ አሁን አገዛዙ ያደረገውን ሳይሆን የትኛውን መስመር እንደሚያቋርጥ እኛም ጠላቶቻችንም የምናውቀው የሚያውቁት ሃቅ ነው።

ለማንኛውም የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ለአገዛዙ ሴራ ተባባሪ ሳይሆን የመብራት መስመሮቹን ለመጠገን ፍላጎቱ ካለው፣ በሁሉም አካባቢ ያሉ ፋኖዎቻችን አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግና ከለላ ለመስጠት ዝግጁዎች መሆናቸውን እንገልፃለን።

ይህ በሆነበት ሁኔታ መስመሮቹ በቶሎ ካልተጠገኑ የሴራው ባለቤት የሆነው አገዛዙ ድርጊቱን ለመፈፀሙ የእምነት ቃል እንደሆነ ይቆጠራል።

ፋኖ ማርሸት ፀሐው የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ!