
ከ 5 ሰአት በፊት
ባንግላዴሽ የሚገኝ አንድ የሕክምና ኮሌጅ አስተማሪ የሆነው ግለሰብ ተማሪ በጥይት መምታቱን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር ዋለ።
አስተማሪው ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ቢውልም ከሥራ የታገደው ግን ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።
ራይሀን ሼሪፍ ከሥራው የታገደው ተማሪዎች ረቡዕ ዕለት ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ ነው።
በጥይት የተመታው ተማሪ ቀዶ ጥገና የተደረገለት ሲሆን አሁንም ሆስፒታል እንደሚገኝ ተሰምቷል።
ቢቢሲ ዶክተር ሻሪፍን ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ጠበቃ እስኪሰየምለት ድረስ ለመገናኛ ብዙኃን ቃሉን መስጠት አልቻለም።
የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የ23 ዓመቱ ተማሪ አሚን ቶማል የቃል ፈተና ላይ ሳለ ነው ከዶክተር ሻሪፍ ጋር እሰጥ-አገባ ውስጥ የገባው።
ይህ የሆነው ሰሜን-ምዕራብ ባንግላዴሽ በምትገኘው የሲራጅጋንጅ ቀጣን ከሚገኝ የሕክምና ትምህርት ቤት ውስጥ ነው።
ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ፈተና አዳራሹ ሽጉጥ ይዘው የመጡት አስተማሪ፤ ተማሪው ላይ ከደገኑበት በኋላ ቀኝ እግሩን መትተውታል።
- ማይክ ሐመር በፕሪቶሪያው ስምምነት፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ላይ ግጭቶች ሊወያዩ ነውከ 6 ሰአት በፊት
- ሁቲዎች በቀይ ባሕር የምታልፍ መርከብን መትተው ሦስት መርከበኞችን መግደላቸው ተዘገበከ 6 ሰአት በፊት
- ‘ባርቢኪው’ – ሄይቲን እያሸበረ ያለው የቀድሞው የፖሊስ መኮንን፤ የአሁኑ የወሮበሎች ቡድን መሪከ 6 ሰአት በፊት
ነገር ግን ጥይቱ ኪሱ ውስጥ የነበረውን ተንቀሳቃሽ ስልክ በመምታቱ ሕይወቱን አደጋ ላይ ከሚጥል አደጋ መትረፍ ችሏል ሲል ዴይሊ ስታር የተሰኘው የባንግላዴሽ ጋዜጣ ፖሊስን ዋቢ አድርጎ ፅፏል።
ዳካ ትሪቢዩን የተባለው ጋዜጣ ደግሞ አስተማሪው ተማሪውን በጥይት ሲመቱት ክፍሉ ውስጥ 45 ተማሪዎች ነበሩ ብሏል።
ተማሪዎች አስተማሪውን ከበው ሌላ አደጋ እንዳያደርስ ካደረጉት በኋላ ተማሪው እርዳታ እንዲያገኝ ወደ ሆስፒታል ወስደውታል።
ከዚህ ክስተት በኋላ ዶክተር ሻሪፍ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል።
የፖሊስ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ዶክተር ሻሪፍ ተማሪውን የመታበት ሽጉጥ “የተመዘገበ አይደለም።”
የሀገሪቱ ፖሊስ አክሎ እንደጠቆመው አስተማሪው በቁጥጥር ሥር ሲውል 82 ጥይቶች፣ አራት ካርታዎች እና 10 ሰንጢዎች ቦርሳው ውስጥ ተገኝተዋል።
ዶክተር ሻሪፍ ብዙውን ጊዜ የጦር መሣሪያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ወደ ትምህርት ቤት ይዞ በማምጣት በትምህርት ወቅት ለተማሪዎች በማሳየት ይታወቃል።
አስተማሪው ወዲያውኑ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ነገር ግን ከትምህርት ቤቱ የታገደው ከሁለት ቀናት በኋላ መሆኑ ባንግላዴሻዊያንን አስቆጥቷል።
የሕክምና ኮሌጅ ተማሪዎች ዶክተር ሻሪፍ እንዲባረርና ቅጣት እንዲተላለፍበት በመጠየቅ ተቃውሞ ሰልፍ ካደረጉ በኋላ ነው አስተማሪው የታገደው።
ፖሊስ ምን እንደተፈጠረ ለማጣራት ልዩ መርማሪ ኮሚቲ ማቋቋሙን አስታውቋል።
የጦር መሣሪያ ባለቤት መሆንና ጥቅም ላይ ማዋል ጥብቅ በሆነባት ባንግላዴሽ መሰል ዜና እምብዛም አይሰማም።