ማዕድን አውጭዎች

ከ 5 ሰአት በፊት

የአሜሪካ የፌደራል ፍርድ ቤት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በማዕድን ማውጣት ሥራ የተሰማሩ አምስት ኩባንያዎች በህጻናት ላይ የጉልበት ብዝበዛ ያደርሳሉ በሚል የቀረበውን ክስ ውድቅ አድርጎታል።

ክስ የቀረበባቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አፕል፣ ማይክሮሶፍት፣ ቴስላ፣ ዴል ቴክኖሎጂ እና የጉግል ቤተሰብ ኩባንያ የሆነው አልፋቤት ናቸው።

ክሱ የቀረበው በዋናነት እነዚህ ኩባንያዎች የኮባልት ምርት ስለሚገዙ በህጻናት የጉልበት ብዝበዛው ላይ ተሳትፎ አላቸው የሚል ነው።

ሆኖም ግን ፍርድ ቤቱ ኩባንያዎቹ የኮባልት ማዕድንን መግዛታቸው የህጻናት የጉልበት ብዝበዛው ላይ ተሳትፈዋል ለሚለው ማረጋገጫ አይደለም በሚል ነው ባለፈው ማክሰኞ ክሱን ውድቅ ያደረገው።

በተጨማሪም ዳኛ ኒኦሚ ራኦ ክሱን ያቀረቡት አካላት ተከሳሾ ኩባንያዎች በማዕድን ማውጫው ውስጥ የሚፈጸመውን የጉልበት ብዝበዛ ለማስቆም ተጽእኖ ነበራቸው ወይ የሚለውን ማሳየት አልቻሉም ብለዋል።

ክስ ያቀረቡት አካላት ግን ውድቅ የተደረገው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የመጨረሻ እንደማይሆን ። በድጋሚ አቤቱታ አቅርበው በኩባንያዎቹ ላይ እርምጃ ለማስወሰድ እንደሚሠሩ የከሳሾቹ ጠበቃ ቴሪ ኮሊንግስዎርዝ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ክሱ የተመሰረተው በ2019 (እአአ) በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አማካኝነት ነበር። በወቅቱ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኮባልት ማዕድን ሲያወጡ በተጎዱ ሕጻናት እና በሞቱ ሰዎች ላይ መነሻ አድርጎ ነበር ክሱ የተመሰረተው።

ሆኖም ግን ይህ ክስ ለሁለት ዓመት ሲካሄድ ከቆየ በኋላ በ2021 በታችኛው ፍርድ ቤት ውድቅ ቢደረግም ይግባኝ ተጠይቆበታል።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የዓለምን 60 በመቶ የኮባልት ማዕድን ታመርታለች። ይህ ማዕድን ለኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ሁነኛ ግብዓት ነው።

እንደ አሜሪካ የሠራተኛ ሚኒስቴር ሪፖርት ከሆነ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኮባልት ማዕድን ቁፋሮ የሚሳተፉ 25 ሺህ ህጻናት ያሉ ሲሆን አብዛኞቹም በአደገኛ ሁኔታ እንደሆነ ገል