በኢትዮጵያ አሁን ያለው የሰላም ዕጦት፣ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር እንደማያስችል የገለጹ ስምንት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ በቅድሚያ ግጭቶች መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡ ድርጅቶቹ፣ የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን አስመልክተው ባወጡት ያጋራ መግለጫ፣ መንግሥት ከግምት ማስገባት ይኖርበታል ያሏቸውን ምክረ ሐሳቦች አቅርበዋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት፣ “ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጽሟል የተባለ…