March 12, 2024 – Konjit Sitotaw 

በደቡብ ኦሞ የሚነገሩት የኦንጎታ እና የባጫ ቋንቋዎች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

Ongota  and Bacha Language in Ethiopia

Ongota and Bacha Language in Ethiopia

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በደቡብ ኦሞ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ባህልና ቋንቋዎች ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የምክክር መድረክ በጂንካ ያካሄደ ሲሆን በደቡብ ኦሞ የሚነገሩት የኦንጎታ እና የባጫ ቋንቋዎች የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው በመድረኩ ተገልጿል።

በየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉት 32 ብሔረሰቦች መካከል 16ቱ በአሪና ደቡብ ኦሞ የሚገኙ እንደሆኑ ሲገለፅ ኦንጎት ከአምስት በማይበልጡ የብራይሌ ብሔረሰብ አባላት ብቻ የሚነገር ሲሆን ፥ የባጫ ብሔረሰብ የሚናገሩት ቋንቋም የመጥፋት አደጋ ከተደቀነባቸው የደቡብ ኦሞ ቋንቋዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በመሆኑም ማህበረሰቡ የአፍ መፍቻ ቋንቋዎችን ለትውልዱ ለማስተላለፍ በቀዳሚነት ኃላፊነት እንዳለበት በማንሳት የመንግሥትና የትምህርት ተቋማትም ቋንቋዎች ተሰንደው እንዲያድጉ በጋራ መሥራት እንደሚያስፈልግም ነው የተለገለው።