ምንሊክ ሳልሳዊ ፡ ልማት ሳይሆን ታሪክን እና ነባር ነዋሪን የማጥፋት ሂደት ነው። ልማት ካለሕዝብ ምንም ፋይዳ የለውም። በቅርስነት የተመዘገቡ በሙሉ እየፈረሱ ነው።
ነጋዴዎች የንግድ ድርጅታቸው ከፈረሰባቸው ቦታ ላይ መልሰው ማልማት እንደማይፈቀድላቸው ተነግሯቸዋል። እናንተ ኖራቹበታል እኛ በተራችን እንኖራለን የሚል የፖለቲካ ንግግር ተንሰራፍቷል።
በሕጋዊነት ስም ሕገወጥ ተግባር በልማት ስም ዜጎችን የማፈናቀል ተግባር እንዲሁም የመሬት ወረራና ውንብድና እየተካሄደ ነው። በዜጎች ላይ መንግስታዊ ሽብርን ያማካለ የፖለቲካ አላማና የዲሞግራፊ ቅየራ ነው።
በነዋሪው እድገት ላይ ምንም ለውጥ ያላመጣ አገዛዝ በየትኛው ሞራሉ ከተማን ማሳመር ይችላል ? ነባሩን ነዋሪ ደሃውን ሜዳ ላይ ወርውሮ የጊዜውን ሰዎች መሬት ማደል የከተማ ለውጥ ማምጣት አይቻልም።
ከተማው ላይ ነዋሪውን የሚያሰፍርና ተጠቃሚ የሚያደርግ ልማት ሊፈጠር ሲገባ መሬቱን ሰብስቦ የፖለቲካ ስልጣንን ተጠቅሞ ሕዝብን ማፈናቀል ነገ ከተጠያቂነት አያስመልጥም። የአዲስ አበባን ሕዝብ ያላሳተፈ ማሕበራዊ ትስስሩን የሚያፈርስ ሆን ተብሎ የሚካሄድ የጥፋት ዘመቻ ነው።
ዜጎች ዛሬም ነገም መጭውን ጊዜ ሁሉ መብታቸውን ይጠይቃሉ፤ ይህ የማይቀር ሃቅ ነው። #MinilikSalsawi