
ከ 4 ሰአት በፊት
ከሰሜን እስከ ደቡብ በሚገኙ በርካታ የአፍሪካ አገራት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ።
አገልግሎቱ ከተቋረጠባቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ላይቤሪያ፣ ጋና እና ቡርኪና ፋሶ ይገኙበታል።
በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ መረጃ የሚሰጠው ክላውድፍሌር ራዳር የተሰኘ ተቋም ከሰሜን እስከ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አገራት በተመሳሳይ ሰዓት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟቸዋል ብሏል።
የሳይበር ደኅንነት እና የኢንተርኔት ግንኙነትን የሚከታተለው ኔትብሎክስ በአይቮሪ ኮስት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ አራት በመቶ መውረዱን ገልጿል።
ኔትብሎክስ ክፍተኛ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከቀነሰባቸው የምዕራብ አፍሪካ አገራት መካከል ቤኒን፣ ላይቤሪያ እና ጋና ይገኙበታል ብሏል።
የደቡብ አፍሪካው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢው ቮዳኮም ደንበኞቹ የአገልግሎት መቆራረጥ እያጋጠማቸው ነው ብሏል። ተቋሙ የችግሩ መንስዔ ባሕር ውስጥ በተዘረጋ ገመድ ላይ ባጋጠመ ችግር ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።
- የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር ተፈቱ14 መጋቢት 2024
- በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ታላላቅ ውድድሮች ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብስክሌት ብሔራዊ ቡድን ፈተናከ 5 ሰአት በፊት
- እስራኤል ሐማስን ‘ለመደምሰስ’ እያካሄደች ያለው ዘመቻ እንዳሰበችው እየተሳካላት ነው?ከ 5 ሰአት በፊት
የላይቤሪያ መንግሥት ደግሞ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከሐሙስ ንጋት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን አስታውቋል።
የላይቤሪያ ዜጎች መሠረታዊ የኢንተርኔት አገልግሎትን እንዲሁም ማሕበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም ሳይችሉ ቀርተዋል።
የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ በንግድ ስራዎች እና በዓለም አቀፍ የገንዘብ ዝውውር ላይ እክል ተፈጥሯል።
ፋቱማ ቤሪ የተባለች ነጋዴ በአገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ገንዘብ በሞባይል አማካይነት መቀበል እንዳልቻለች ለቢቢሲ ተናግራለች።
ቤንጃሚን ጋርካፓህ የተባለ የላይቤሪያ መዲና ሞኖሮቪያ ነዋሪ ደግሞ “50 በመቶ የሆነው ሕይወቴን እንዳጣው ተሰምቶኛል” ብሏል።
የላይቤሪያ የቴሌኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ከአውሮፓ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ከባሕር ስር በተዘረጋው የኢንተርኔት ገመድ ላይ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
የጋና የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን በተመሳሳይ ለአገልግሎቱ መቋረጥ ምክንያቱ ባሕር ውስጥ ያለው የኢንርኔት ገመድ ነው ብሏል።
በከፍተኛ ደረጃ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ካጋጠማቸው አገራት መካከል ዘ ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጋና፣ ቤኒን እና ኒጀር እንደሆኑ ክላውድፍሌር በማሕበራዊ ድረ-ገጹ ላይ አስታውቋል።