March 15, 2024 – Konjit Sitotaw
አሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የግጭትና መረጋጋት ረዳት ሚንስትር የኾኑት አን ዊትኮውስኪ ከመጋቢት 8 እስከ 17 በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሞዛምቢክ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ።
ረዳት ሚንስትሯ በኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚኖራቸው ቆይታ፣ አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን ለቀጠናዊ ጥረቶች የምታደርጋቸውን ጥረቶች ለማጠናከር ያለመ ውይይት እንደሚያደርጉ መስሪያ ቤታቸው ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።
ረዳት ሚንስትሯ፣ በሦስቱ አገራት ከመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ከሲቪል ማኅበረሰብና ከዓለማቀፍ አጋሮች ተወካዮች ጋር የግጭት ተጎጂ ማኅበረሰቦችን መልሶ ለማቋቋም በማደረጉ ጥረቶች ዙሪያ ጭምር እንደሚወያዩና አሜሪካ በዚኹ መስክ ለሦስቱ አገራት እያደረገች ያለችውን ድጋፍ እንደሚገመግሙ ተገልጧል