March 15, 2024 – Konjit Sitotaw 

18 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ ዋጅር ተያዙ

በኬንያ ዋጅር ካውንቲ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ ገብተዋል የተባሉ 18 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዋጅር ፖሊስ ገልጿል።

18ቱ ፍልስተኞች የተያዙት በዛሬው እለት ኮሮንዲሌ በሚባል የከተማይቱ አውራጃ በተደረገ ኦፕሬሽን መሆኑ ተነግሯል።

ፍልሰተኞቹ በኮሮንዲሌ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ሲሆን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ በመግባት ክስ እንዲመሰረትባቸው የሚያስችለውን ሂደት በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ ተጠቁሟል።

በኬንያ በህገ-ወጥ መንገድ ገብተው የተገኙ የሌላ ሀገር ዜጎች የመባረር ወይም እስራት ሊገጥማቸው እንደሚችል ሲገለፅ በተጨማሪም፣ በኬንያ የኢሚግሬሽን ህጎች በተገለፀው መሰረት ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችልም ነው የተገለፀው።