March 15, 2024 – Konjit Sitotaw
በአፋር ክልል በኢሳ እና አፋር ጎሳዎች መካከል ግጭት መቀጠሉ ተሰምቷል ።
ትናንት በአፋር ክልል ዞን 6 ወይም ማሂ ረሱ ዞን ውስጥ በሚገኘውና አፋር እና ሶማሌ ክልሎች በሚወዛገቡበት አዳዶ ወረዳ በኹለቱ ጎሳዎች መካከል ግጭት ማገርሸቱን ምንጮች ተናግረዋል።
በኹለቱ ጎሳዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተደጋጋሚ ግጭቶች የተከሰቱ ቢኾንም፣ ኹለቱ ክልሎች ግን ስለ ጎሳ ግጭቶች መግለጫ ሲያወጡ አይሰሙም።
የጎሳ ግጭቱ ትናንት በድጋሚ ያገረሸው፣ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስተባባሪነት የኸለቱ ክልሎች የጎሳ እና የአገር ሽማግሌዎች ተገናኝተው ከመከሩና ለግጭቶችና አለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ ለመፍታት ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሚመራው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ካቋቋሙ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
ዋዜማ ራዲዮ