March 16, 2024 – Konjit Sitotaw

የአሜሪካ ዓለማቀፍ ተረድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ትናንት በድጋሚ በመቀሌ ጉብኝት አድርጓል።

በሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ የዋና ዳይሬክተሯ ረዳት ሶናሊ ኮርዴ የመሩት ልዑካን ቡድን፣ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊዎች ጋር በክልሉ በተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስና በወቅታዊ ኹኔታዎች ዙሪያ መክሯል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ አፋር ክልልም አቅንቶ፣ የዕርዳታ ሥርጭት ሂደቱን ተመልክቷል።

ከጥር ወር ወዲህ፣ ድርጅቱ በትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ለ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ተረጂዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ማቅረቡን ገልጧል።