March 16, 2024 – Konjit Sitotaw 

የኤርትራ መንግሥት፣ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ዋና ጸሃፊ ኤሊዜ ኪሪስ “ኤርትራ ሕግ የሌለባት አገር ናት” በማለት በተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በቅርቡ መናገራቸውን አጣጥሎታል።

የኤርትራ መንግሥት፣ ረዳት ዋና ጸሃፊዋ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ እንደሚገኙ መግለጣቸው፣ አውቀውም ኾነ ሳያውቁ የዓለማቀፉን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ አለመቀበላቸውን ያሳያል በማለት ተችቷል።

ሃላፊዋ ያወጡት መግለጫ፣ ያልተረጋገጡና ሐሰተኛ መረጃዎችን ያካተቱ እንደኾነም ኤርትራ ጠቅሳለች።

የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዓለማቀፍ ወንጀል ፈጽማ የማታውቀውን ኤርትራ ለቀቅ አድርጎ፣ በሌሎች የዓለም ክፍሎች ለሚፈጸሙ ዓለማቀፍ የመብት ጥሰቶች ቅድሚያ ቢሰጥ ይሻላል በማለትም ኤርትራ መክራለች።