
ከ 5 ሰአት በፊት
ከጥቁር ዛምቢያዊት እናት እና ከነጭ የዌልስ አባት የተወለዱት ቮውን ገተን የመጀመሪያው ጥቁር የዌልስ መሪ ሊሆኑ ነው።
ቮውን ገተን በዌልስ ሠራተኞች ፓርቲ የአመራር ምርጫ 51.7 በመቶ ድምጽ በማግኘት ተቀናቃኛቸውን በጠባብ ድምጽ አሸንፈዋል።
የገተን ተፎካካሪ የነበሩት ጄሬሚ ማይልስ 48.3 በመቶ ድምጽ አግኝተዋል።
ቮውን ገተን በአሁኑ ወቅት የዌልስ ተቀዳሚ ሚኒስትር የሆኑትን ማርክ ደሬክፎርድን በመተካት የፊታችን ማክሰኞ ስልጣን ይረከባሉ።
ገተን የፓርቲያቸውን የአመራር ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከዩናይትድ ኪንግደም ሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪየር ስታርመር እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የእንኳን ደስ ያሎት መልዕክት ደርሷቸዋል።
የ50 ዓመት የልደት በዓላቸውን ከትናንት በስቲያ አርብ ያከበሩት ቮውን ገተን የሕግ ሥራቸውን ትተው የፖለቲካውን ዓለም የተቀላቀሉት እአአ 2011 ላይ የዌልስ ፓርላማ አባል ከሆኑ በኋለ ነው።
- የወንድ ዘር ፍሬ እና የሴት እንቁላል ልገሳ በኢትዮጵያ: ለመካንነት አዲስ መፍትሔ?16 መጋቢት 2024
- የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዋን ወደ ትልቅ ቢዝነስ የሸጋገረች ኢትዮጵያዊትከ 6 ሰአት በፊት
- የዩናይትድ አየር መንገድ ቦይንግ አውሮፕላን አንድ አካሉ ጠፍቶበት ምንም ጉዳት ሳይደርስበት አረፈከ 5 ሰአት በፊት
ገተን በተቀዳሚ ሚኒስትር ዴክፎርድ ካቢኔ ውስጥ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
ገተን የፓርቲ አመራር ምርጫን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ባደረጉት ንግግር ተሰናባቹን ተቀዳሚ ሚንስትር እንዲሁም ተቀናቃቸው የነበሩትን ጄሬሚ ማይልስን አመስግነዋል።
ድላቸውን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር፤ “ዛሬ በዌልስ ታሪክ አዲስ ታሪክ ተጽፏል” ካሉ በኋላ በመላው በአውሮፓ ብቸኛው ጥቁር መሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
3 ሚሊዮን ገደማ የሚሆን ሕዝብ ያላት ዌልስ ዩናይትድ ኪንግደምን ከሚፈጥሩ አራት አገራት መካከል አንዷ ነች።
እአአ 2021 ላይ በዩኬ በተካሄደ ቆጠራ ከአጠቃላይ የዌልስ ሕዝብ እራሱን ጥቁር ብሎ የሚገልጽ ነዋሪ ከ1 በመቶ በታች ነው።