March 19, 2024 – Konjit Sitotaw
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የስነ ሕዝብ፣ ስደትና ፍልሰት ረዳት ሚንስትር ጁሌይታ ኖይስ ትናንት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ኖይስ፣ ትናንት ከተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊ ራሚዝ አላክባሮቭ እና ከሌሎች የተመድ ሃላፊዎች ጋር ተመድ ለተረጂዎች በሚያቀርባቸው ሰብዓዊ ድጋፎች ዙሪያ መወያየታቸውን በ”ኤክስ” ገጻቸው ገልጸዋል።
ረዳት ሚንስትሯ ዛሬና ነገ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናትና ዓለማቀፍ አጋሮች ጋር ስደተኖችን በሦስተኛ አገራት በማስፈር፣ በሰብዓዊ ዕርዳታ፣ ረድዔት ሠራተኞችን ከጥቃት በመጠበቅና ኢትዮጵያ ባለፈው ታኅሳስ ጀኔቫ ላይ በገባቻቸው የስደተኞች ቃል ኪዳኖች ዙሪያ ይወያያሉ።