March 19, 2024 – Konjit Sitotaw
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በተያዘው ዓመት ምንም ስኳር አለማምረቱን የመንግሥት ዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ፋብሪካው ስኳር ያላመረተው፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጩ የኾነው የቁንዝላ ኃይል ማመንጫ ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ብልሽት ስለገጠመውና በፋብሪካው ላይ የማሽን አቅርቦት እጥረት በመፈጠሩ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።
ፋብሪካው ዘንድሮ 183 ሺህ ኩንታል ስኳር እንዲያመርት ታቅዶ የነበረ ሲኾን፣ ከጅምሩ ሲገነባ ግን በቀን 12 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም እንዳለው ተገልጦ ነበር።