March 21, 2024 – Konjit Sitotaw
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካው የጆ ባይደን አስተዳደር በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች “ፍትህና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ምንም ዓይነት አዲስ የፖሊሲ ለውጥ አላደረገም” በማለት ተችቷል።
አምነስቲ፣ አሜሪካ ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙና ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንድትደግፍ ጠይቋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከንም፣ ፍትህ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን በጦርነቱ የጦር ወንጀልና በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል በማለት ቀደም ሲል ያሳለፉትን ብያኔ እንዲያድሱ አምነስቲ ጠይቋል።
ብሊንከን ከአፍሪካ ኅብረትና ከዓለማቀፉ ኅብረተሰብ ጋር በመተባበር ሠራዊቱ በአማራ ክልል ሲቪሎችን ዒላማ ማድረጉን መንግሥት እንዲያስቆም እንዲጠይቁም ጥሪ አድርጓል።
አምነስቲ፣ ብሊንከን በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በሚካሄዱ የትጥቅ ግጭቶች በሚፈጸሙ ጥሰቶች ላይ የዓለማቀፍ ወንጀል ብያኔ እንዲሰጡም ጠይቋል።