
አዲስ አበባ ማኅበራዊ ንቅናቄ
ሕዝብን ማታለል፣ እንደቀድሞ እየዋሹ መኖር የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል።
ከአዲስ አበባ ማኀበራዊ ንቅናቄ (#አማን) የተሠጠ መግለጫ
በአዲስአበባ ሳር ቤት አካባቢ በአማንና አራዳ የመንግስት ሠራተኞች ክፍል መጋቢት 11/2016 ዓ.ም በሠራተኞች ማጓጓዣ (public bus) ላይ የተወሰደውን ጥቃት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሊያስተባብል ሞክሯል። ይህ ከማኀበረሰቡ የተነጠለ፣ የሕዝብ ጠላት ለሆነው አገዛዝ ወንበር ጠባቂ የሆነ ክፍል በቀን የተፈጸመን ጥቃት፣ ሕዝብ የተመለከተውን ክስተት አልተፈጸመም ብሎ ሊክድ ሞክሯል።
በመሠረቱ ጥቃቱና እንቅስቃሴው ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነ እንዳልሆነ ፖሊስ ጠንቅቆ ያውቃል። ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ ዋና ቢሮ አጠገብ የአማን ወረቀት መበተኑ እንዴት እንዳስደነገጠው እናውቃለን። አራት ኪሎ አማን ፋኖንና ሌሎች አጋሮቹን ጨምሮ ኢትዮጵያ ተነሽ ማለታችንን ተከትሎ ፖሊሶችና የመከላከያ አባላቱ ላይ ምን አይነት እርምጃ እንደወሰደ እኛም እናውቃለን። እነሱም ያውቃሉ።
ገለልተኛና ሕዝባዊ መሆን የነበረበት ይህ አካል ለመጣው ለሄደው ሁሉ መንበርከኩን ቀጥሎ ለአዳነች አበቤ ፀረ-ሕዝብ አገዛዝ ጉልበቱ እስኪላጥ ተንበርክኮ ጥቂት የቀረችውን ስሙን አጥቶአል። ዛሬ ለስሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ በእውነታው ግን ለቅኝት የሚመደቡ ተራ ፖሊሶችን ሳይቀር በብሄረሰብ ኮታ እየመደበ የሚገኝበት የአለመተማመን ደረጃው በአፍጢሙ ሊደፋው፣ የፍርሀት መጠኑ በአናቱ ሊተክለው የደረሰ አካል ሆኗል።
የሕዝብን ቁጣ፣ የአዲስ አበቤን መነዴት በክህደታቹ ልትሸፍኑት አትችሉም።ዛሬ የደረስበት መንገፍገፍ፣ የደረስንበት ቁጣ ቢሯችሁ ድረስ እንድንገባ አድርጎናል። ለነገ ታሪካቹ በእውነት የምታስቡ ከሆነ አይን ያወጣ ውሸታችሁን ትታችሁ ከህዝባችሁ ጎን ቁሙ፣ ሀገር ለማፍረስ ከሚተጋ አረመኔ ስርዓት አትተባበሩ። ይህ ብቻ ነው ለጥፋታቹ ስርየት፣ ለኃጢአታችሁ ንስሃ የሚሆነው። ከዚህ ውጭ መንገድ የለም። ወይ ሕዝባዊነት፣ ወይንም ሕዝብና ሀገርን ክዶ ከአገዛዙ ጋር መቆም።
ይህን የካዳችሁትን የመንግስት ሠራተኛውን ቁጣ የንቅናቄያችን የሠራተኛ ክፍል በቀጣይነት ምን ደረጃ እንደደረሠ ሊያሣይ ቃል ይገባል።
የአዲስ አበባ ማኀበራዊ ንቅናቄ (#አማን)
ሕዝባዊነት ያሸንፋል