
ከ 7 ሰአት በፊት
እንግሊዛዊቷ ጃስሚን ፓሪስ ከዓለማችን ከባድ የሩጫ ውድድሮች ቀዳሚው ነው የሚባለውን በመጨረስ የመጀመሪያዋ ሴት ሆነች።
ይህ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍነውን እና 18 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ተራራን መውጣት እና መውረድ የሚጠይቀውን ውድድር ከ60 ሰዓት ባነሰ ግዜ ውስጥ መጨረስ ችላለች።
ጃስሚን በርክሌይ ማራቶንስ የተባለውን ውድድር በ60 ሰዓታት ውስጥ የመጨረስ ግዴት የነበረባት ሲሆን ይህን ከባድ ሩጫ ለመጨረስ ከተሰጣት 60 ሰዓታት፤ 1 ደቂቃ ከ 39 ሴኮንዶች ብቻ ሲቀራት ውድድሩን ጨርሳለች።
በውድድሩ መጨረሻ ላይ ከፍተኛ ድካም ውስጥ የነበረችው ሴት የመጨረሻ መስመሩን እንዳለፈች ተዝለፍልፋ ወድቃለች።
ከእአአ 1989 ጀምሮ ወንዶችን ጨምሮ እስካሁን ድረስ ይህን ውድድር ከ60 ሰዓታት በታች መግባት የቻሉት 20 ሰዎች ብቻ ናቸው።
- የ133 ሰዎች ሕይወት በቀጠፈው የሞስኮው ጥቃት የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች መያዛቸውን ፑቲን አስታወቁከ 3 ሰአት በፊት
- ከ200 በላይ ታጋቾችን ተደራድሮ ያስለቀቀው ናይጄሪያዊከ 9 ሰአት በፊት
- ቀጣዩ ጄምስ ቦንድ ማን ሊሆን ይችላል?ከ 9 ሰአት በፊት
የ40 ዓመቷ ጃስሚን ውድድሩን ለመጨረስ ተራራ መውጣት እና መውረድ፣ በጨለማ ጫካ እና ጢሻ ውስጥ መሮጥ ነበረባት።
ከውድድሩ በፊት ጃስሚን በአንድ ወቅት “በርክሌ ማራቶንስን ስለመሮጥ ባለፉት ዓመታት ሳስበው የቆየሁት ነገር ነው። በጣም ከባድ እንደውme ጭራሽ የማይችል ሊሆን እንደሚችል አውቃለሁ። ነገር ግን የማይቻል ሊሆን እንደሚችል ማሰቤ ውድድሩን እንዳደርግ ፍላጎት አሳድሮብኛል” ብላ ነበር።
የዚህ ውድድር ጽንሰ ሐሳብ የመጣው እአአ 1977 ላይ ጄምስ ኤርል ሬይ የተባለ እስረኛ ከእስር ያመለጠበት ሁኔታ ላይ በመመርኮዝ ነው።

በማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ግድያ ታስሮ የነበረው ጄምስ፤ ብሩሺይ ማውንቴን ከተባለ እስር ቤት ካመለጠ በኋላ ረዥም ርቀት ባይሸፍንም በጫካ ውስጥ ከፖሊስ ለማምለጥ ለ50 ሰዓታት ሮጦ ነበር።
ጃስሚን ከበርክሌ ማራቶንስ በፊትም ሌላ ከባድ የጎዳና ላይ ሩጫ በማሸነፍ ጭምር ታሪክ ሰርታለች።
የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ጀስሚን እአአ 2019 ላይ የ430 ኪሎ ሜትር ሩጫን 83 ሰዓት ከ12 ደቂቃ በመግባት ከዚህ ቀደም ተይዞ የነበረውን ሬኮርድ በ12 ሰዓታት ማሻሻል ችላ ነበር።
በወቅቱ ከጃስሚን ድል ጋር ተያይዞ በስፋት የተወራው ይህች እናት ጨቅላ ለነበረው ልጇ በሩጫዋ መካከል የጡት ወተት አልባ መስጠቷ ነበር።