March 25, 2024 

ዝቋላ ድጋሚ ሥጋት ገጥሞታል

በቅርቡ መነኮሳቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት የደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መጠነኛ ጥበቃ ሲሰጠው የነበረው መከላከያ ትናንት እሑድ ገዳሙን ለቅቆ በመውጣቱ ድጋሚ ሥጋት ላይ መውደቁን የተላከልን መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በፊት ከመንግሥት ጋር በነበሩት ውይይቶች ገዳሙ ከሥጋት ነጻ የሚሆንበት ሥራ እንደሚሠራ ስምምነት ላይ መደረሱ የሚታወስ ሲሆን ምክንያቱ ለጊዜው ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ የመከላከያ ሠራዊቱ በምሽት ገዳሙን ለቅቆ መውጣቱ ማኅበረ መነኮሳቱ ላይ ከፍተኛ ሥጋት ፈጥሯል።

“የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡ እናሳስባለን” ብሏል ገዳሙ። (አደባባይ ሚዲያ)