March 25, 2024 – Konjit Sitotaw 

የፍትሕ ተቋማት በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ላይ ክስ እንዲመሰረት አያደርጉም- የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

የፍትሕ አካላት ለሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ስራዎች የማይተባበሩ የመንግስት አሰፈጻሚ አካላት ላይ ክስ እንዲመሰርት አይተባበሩም ሲል ተቋሙ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአቤቱታ ቅበላ፣ ምርመራና የመፍትሄ ሀሳብ አፈጻጸምን በተመለከተ ባደረገው ውይይት እንደተገለጸው ከተቋሙ ክስ እንዲመሰረት ጥያቄ ቢቀርብም ተባባሪ ያለመሆን ችግሮች አሉ።

ዋና እንባ ጠባቂ እንዳለ ኃይሌ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ህገመንገስት አንቀጽ 37/1 ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት ወይም በሌላ በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል ጉዳዩን የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት እንዳለው ይደነግጋል ብለው የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ላይ ግን እየተፈጸመ እንዳልሆነ አመላክተዋል።

ዋና ዕንባ ጠባቂው የዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብት ሲጓደል ሕዝብ በመንግስት ላይ ያለው አመኔታ እንደሚሸረሸር ገልጸዋል።

በመንግስት አስፈጻሚ አካላት ላይ የሚደርሰውን የአስተዳደራዊ በደል ችግሮች በዋነኛነት ለመቅረፍ ተጠያቂነት መረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ተሰጥቷል።