ነአመን ዘለቀ ፡ የፕያሳን ነዋሪ አዲስ አበቤ ለንቅለ ተከላ ግባቸው አፈናቀሉት፣ ማህበራዊ ትስስሩን ናዱት። ቅርሶችን አፈረሱ። በዛሬው ዜጎችን ማፈናቀል፣ ታሪክና ቅርስ ማውደም፣ በፒያሳ እንደማያቆሙ ባለፉት ጥቂት አመታት የአብይ አህመድና የኦሮሚያ ብልጽግና በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የፈጸሟቸው የክፋት፣ የመሰሪነት፣ የዘረኝነትና፣ የአግላይነት፣ ጸረ ደሃም ተግባራት ያረጋግጣሉ። ያለምንም ይሉኝታና ሀፍረት፣ ለዜጎች ርህራሄ አልባ ግፍ እንዲፈናቀሉ የተደረጉ መቶ ሺዎች፣”ህጋዊ ድሃ” የተድረጉ፣ ሰው መሳይ አውሬው የሸገር ከተማ ከንቲባ እንደነገረን በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ አካባቢዎች ነዋሪዎችን በግፍ በማፈናቀል የፈጸሙት ይህ ነው የማይባል ግፍና ሰቆቃ በርክታ ማረጋገጫዎች ልባችን እየደማ እይተናል። በየአካባቢው ነባር ሰፈሮችን ማፈስ፣ ማህበራዊ ትስስሮችን መበጣጠስ፣ የአዲስ አበባ አዲስ አበባ ያደረጉ ቅርሶች ማውደምና መሰረዝ፣ ማንነትን መጨፍለቅ ይቀጥላል። አላማው ልማት አይደለም፣ ፓለቲካ ነው’’

በአለማችን የከተማ ልማት አስተሳሰብና ማእቀፍ/ፓራዳም/ፍሬምወርክ ፣ ዘላቂነት፣ ጽኑነት ፣ አካታችት ፣ ፍታዊነት/Environmental sustainability/Climate Resilience/Socially inclusive and just በሚሉ ዋና ዋና ማገሮች የሚመራ እየሆነ ነው፣ ይህም በበርካታ ሀገሮች ገዢ አስተሳሰብና አሰራር እየሆነ ይገኛል ። በ 2050 የአለማችን ህዝብ 70% የከተማ ነዎሪዎች እንደሚሆኑ የበርካታ ጥናቶች ትንበያ ያሳያል። ስለሆነውም ልማት የከተማውን ኢንፍራስታክቸሮች ማስፋፋት ብቻ ሳይሆን ጽኑ፣ ዘላቂ/እንዲሆኑ ፣ ዜጎች ፣ የከተማ ነዋሪዎች ማህበራዊና አካታችነት፣ ፍትሃዊነት፣ ኢኮኖሚ ጽናትና ዘላቂነት/ሶሻል ኢኮኖሚክ ስስተኔብሊቲ/ሬሲሊያንስ እንዲኖራቸው ማድረግን ታሳቢ ያደረገ የልማት አስተሳሰብ ማእቀፍ/ፍሬምወርክ ነው። በመሰረቱ ልማት መዳረሻውም ፣ መነሻውም ሰው ነው። የልማት ግብ የሰዎች፣ የማህበረቦች፣ የዚጎች ልማት ነው፣ የኮንክሪት ጫካ ወይንም ኮንክሪት ጃንግል ግንባታ አይደለም። አብይ አህመድ እንደሚያደርግው የብልጭልጭ ፎቆችና ግንባታዎች መደርደር አይደለም። አማራታ ሰን፣ ማርታ ናስባም ፣ ሌሎችም ታላላቅ የኢኮኖሚ ልማት ፈልሳፎችና ሃሳቢዎች እንዳስቀመጡት፣ ልማት መድረሻውም ፣ መነሻውም የሰው ልጅ ነው። የዜጎችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነ ልቦናዊ አቅም ማጠናከር ፣ ማዳበር ነው። በእርግጥም ለህዝብ ለዜጎች የሚጨነቅና ፣ በእኩልነትም የምያይ መንግስት ካለ አንድ ሃገር ውስጥ፣ ዋነኛ የመንግስት ተግባር ይህን መተግበር ነው። ሰው ተኮር፣ ዜጋ ተኮር ልማት/human centered development and enhancement of human capabilities.
የእነ እብይ አህመድና የአደነች አቤቤ አገዛዝ ከዚህ በተቃራኒው ፣ ማፈናቀል፣ ማውደም፣ ዜጎችን ለማህበራዊ ምስቅልቅ፣ ትርምስ፣ መከራና እንግልት መዳረግ ዋናው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የአዲስ አባባ ህዝብ የሚገኝባቸው አስከፊ ገጽታዎች ሆነዋል። ለልማት ሳይሆን ለፓለቲካ አላማ የሚፈጸም፣ ግፍና በደል። የጥቅም አጋሮቻቸውን በብዙሃን ኪሳራ ላማደለብ የሚፈጸም በደል፣ ኢፍትሃዊነት፣ ጋጠ ወጥነት፣ እብሪትና ትብኢት!!
ፒያሳን ለማፈራረስ ለማውደም የተሄደበት ርቀት ምንም ጥናትም፣ ፍታዊነትም፣ አካታችነትም ፣ ከተሞች ለማዘመን፣ ለማስዋብ ማእክል መደረግ ያለባቸው ዋና ዋና አምዶች ጋር ምንም የማይገናኝ መሆኑ ፣ ጥናትም እለተድረገበትም። ከዜጎች ፣ ከነዋሪዎች ጋር ምክክር ፣ ውይይት አልተደረገበትም። በዘፈቀደ፣ በአብይ አህመድና በባለግዜዎች የተወሰነ ስለመሆኑ ከሰሞኑ የወጡ ልዩ ልዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ’’። የጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረትና ሌሎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተጻፉ “የሆረር ታሪኮች” ያረጋግጣሉ።
የከተሜ የልቦና ውቅር የሌላቸው ፣ አዲስ አበባ ተወልደውም ሆነ አድገው ጣሟን የማያውቁ ፣ በድህነት ውስጥ እድገው ድሃን የሚጠየፉ፣ ወያኔ ከየትም ኮልኩሎ ያመጣቸው የኦሮሞያ ብልጽጋና ካድሬዎችና የአማራ ብልጽግና የሚባለው የተላላኪዎቻቸው ጥርቃሞ ያለምንፍም ሃፍረት “ተመርጠናል” ያሻንን እናደርጋለን በሚል ትብኢትና እብሪት በአዲስ አባባ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ ይቀጥላሉ። እነ አብይ አህመድ የነውረና ፣ ግፈኛ ስብስብ በስልጣን ላይ እንዲቆይ እሰከተፈቀደለት ድረስ የአዲስ አበባ ህዝብ በገዥዎች የተጫነበት ማን አለብኝነት፣ ግፍ፣ በደል፣ ማፈናቀል፣ ማህበረሰብ ትስስር መበጣጠስ፣ ቅርስን ማውደምና መሰረዝ፣ “የሆረር ታሪኮች” ይቀጥላሉ።
የአዲስ አባባ ህዝብ መወሰን እና ማድረግ ያለበት፣ የአብይ አህመድን ግፈኛ ፣ ጋጠ ወጥ ፣ አምባገነናዊ አገዛዝ በሚችለው መንገዶችና ፣ የትግል ስልቶች መገዝገዝ፣ ማሽመድመድ፣ ብሎም ለማስወገድ ፣ መደራጀትና መታገል ነው። በአማራ ክልል የአገዛዙን የጭቆና መዋቅር እያፈራረሰና ፣ ህዝብ በኦሮሞያ ብልጽግና ምስለኔዎችና ተላላኪዎች ሳይሆን ራሱ በመረጣቸው ወኪሎቹ እንዲተዳደር መሰረት እየጣለ የሚገኘው የፋኖ የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ትምህርት መቅሰም አሰፈላጊ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብም የራሱን አደረጃጀት በየአካባቢው በመመስረት ሰገጤ፣ ጋጠ ወጥ፣ ደንቆሮ፣ ግፈኞች አሻፈረኝ፣ በቃኝ አልገዛም ብሎ፣ በልዩ ልዩ የትግል ስልቶች ለማዳከም ራሱን ማደራጀት ይገባል።
====
ከፒያሳ ተነሺዎች የሚደርሱኝ ሆረር ታሪኮች እንደቀጠሉ ነው!
መቼም ከተማ ሳይዘምን፣ ሳይቀየር እና ሳይነካ የትም አለም ላይ አይቆይም። ዱባይ የዛሬ 30 አመት ብትታይ የዛሬውን ትሆናለች ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ነገር ግን፣
– ለልማት እና ለከተማ ለውጥ የሚነሱ ሰዎች ለምን ብዙ ግዜ ‘ሰለባ’ ይሆናሉ? ስንቶች ግቡበት ተብሎ የተሰጣቸውን ለማመን የሚከብድ ‘ቦታ’ (ቤት ለማለት አልደፍርም) በቴሌግራም ልከውልኛል፣ ታድያ እነዚህ ቤተሰቦች ህፃናትን እና አቅመ ደካሞችን ይዘው ውሀ፣ መብራት፣ ሽንት ቤት፣ መንገድ… ወዘተ ያለሌበት ቦታ እንዴት ይኑሩ?
– ተነሱ ሲባል በሳምንታት፣ ካለም በወር ውስጥ ለምን ይሆናል? ቢያንስ ስራም ሆነ ኑሮ ማመቻቸት የሚችል ፋታ እንዲያገኝ ለምን ግዜ አይሰጥም? ጥድፊያው እና እሽቅድድሙ ከምን እና ከማን ጋር ነው? የከተማ ልማቱ፣ እድገቱ እና ማማሩ ለማን ነው? ለህዝብ ከሆነ ህዝብን ያማከለ ለምን አይሆንም?
በዚህ ዙርያ አቶ ሙሼ ሰሙ ባሰፈሩት አንድ ፅሁፍ ይህን ብለዋል፣
– በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ከ200 ሺህ ያላነሱ ነባር ይዞታዎችና ሱቆች እንደሚፈርሱ ይገመታል። ይህ ማለት ከነባር ባለ ይዞታዎቹና ከተከራይ ባለሱቆች ጋር መስተጋብር ፈጥረው የሚሰሩ ደላሎች፣ ጥበቃዎች፣ ጽዳት ሰራተኞች፣ ተቀጣሪ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሰጭዎች ሲደምሩበት ቁጥራቸው ከ500 ሺህ ሊበልጥ ይችላል። ቤተሰቦቻቸውንና ጥገኞቻቸውን ስናክልበት ደግሞ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሊሆኑ ይችላሉ።
ግድ የለም… ሰው፣ ሰውነት እና ሰብአዊነት ከየትኛውም ልማት ይቀድማል። Elias Meseret
ፎቶ: የጥንቷ ፒያሳ