March 25, 2024 – Konjit Sitotaw
” ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል ሙሉውን ኃላፊነት ይወስዳል ” – የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ምን አለ
?
” የአማራ ክልል የትግራይ መሬት በካርታው በማስፈር የትምህርቱ ሰርዓቱ አካል በማድረግ እያስተማረበት ይገኛል ” ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ከሰሰ።
” ክልሉ የትግራይ መሬት በሚመለከት በስርዓተ ትምህርቱ ያሰፈረው ካርታ ኃላፍነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ከፋፍሎ ለማጥፋት ያወጀው ዘመቻ በማስቀጠል በከፋ መልኩ እየሰራበት እንደሚገኝ ማረጋገጫ መሆኑ ተገንዝበናል ” ብሏል።
” የአማራ ክልል መንግስት በህዝባችን ላይ አየፈፀመው የቆየውና አሁንም በሃይል በያዛቸው የትግራይ አከባቢዎች እየፈፀመ የሚገኘው ግፍና መከራ ተሰሞቶት በመፀፀት ፈንታ ወደ ባሰ ታሪካዊ ስህተት መግባቱ በቀጣይነት ዋጋ እንደሚያስከፍለው በማወቅ በአስቸኳይ እርምት ማድረግ አለበት ” ሲል አስስቧል።
ካቢኔው ፤ ” የፌደራል መንግስት ከአሁን በፊት የፌደራል ተቋማት ዛሬ ደግሞ በአማራ ክልል እየተዘጋጁ ያሉ ኃላፊነት የጎደላቸው ካርታዎች እንዲያርማቸውና በጥፋት ፈፃሚዎች ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰድ እየተገባው በዝምታ ማለፉ የጥፋቱ አካል መሆኑ የሚያመላክት ነው ” ብሏል።
” የትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመፈፀም ሰላም እና መረጋጋት እንዲመጣ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ በሚሰሩበት ወቅት ፤ የአማራ ክልል የሰላም ሂደቱ ለማወክ ይህ መሰል ነገር ጫሪ ጥፋት ሆን ብሎ መፈፀሙ ሊሰመርበት ይገባል ” ሲልም ገልጿል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ፥ ” የአማራ ህዝብም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች በአማራ ክልል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ የቆየውና አሁንም የቀጠለው ግፍና በደል ይቁም ብሎ ከትግራይ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጎኑ እንዲቆሙ ” ብሏል።
” ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከተለው ነገር ሁሉ የአማራ ክልል መሉውን ኃላፊነት እንደሚወስድ ለማስታወቅ እንፈልጋለን ” ሲል ገልጿል።