
ከ 3 ሰአት በፊት
የቀደሞው የቻይና እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ቼን ዡዩዋን በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የዕድሜ ልክ አስራት ተፈረደባቸው።
ባለፈው ጥር ፕሬዝዳንቱ 81 ሚሊዮን ዩዋን (11.2 ሚሊዮን ዶላር) በጉቦ መልክ መውሰዳቸውን አምነው ነበር።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ የሚመሩት ፀረ-ሙስና እንቅስቃሴ በስፖርት፣ በባንክ እና በወታደራዊ ዘርፎች በሙስና ውስጥ እጃቸው ያለበት ሰዎችን ዘብጥያ እያወረዱ ነው።
ከዚህም ጋር በተያያዘ በርካታ ተጫዋቾች እና አሠልጣኞች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ ሲካሄድባቸው ቆይቷል።
በማዕከላዊ ቻይና በተካሄደው ችሎት የእግር ኳስ ማኅበሩ ፕሬዝዳንት ከአውሮፓውያኑ 2010 እስከ 2023 ባለው ጊዜ የተሳተፉባቸው የሙስና ወንጀሎች የተዳሰሱበት ነው።
ቼን የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸው በፊት የሻንግሃይ ኢንተርናሽናል ፖርት ግሩፕ ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።
ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ቼን በገንዘብ እና በዓይነት ጉቦ እየተቀበሉ ፕሮጀክቶች ሲሰጡ እና የእግር ኳስ ዝግጅቶችን ሲያመቻቹ ነበር።
- የአሜሪካ ፌዴራል ፖሊስ የራፐር “ዲዲ” መኖሪያ ቤቶች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ አደረገከ 8 ሰአት በፊት
- በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዳሳሰባት አሜሪካ ገለጸችከ 5 ሰአት በፊት
- በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሜሪካውያን በቻይና የመረጃ መንታፊዎች ወጥመድ መያዛቸው ተነገረከ 8 ሰአት በፊት
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንደሚለው ግለሰቡ በቻይና እግር ኳስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደርሰዋል ሲል ዢንዋ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የአገሪቱ ቴሌቪዠን ጣቢያ እንደዘገበው ሌሎች ሦስት የእግር ኳስ ባለሥልጣናትም ከ8 እስከ 14 ዓመታት እስር ተፈርዶባቸዋል።
ከጥቂት ወራት በፊት የቀድሞው የኤቨርተን አማካይ እና የቻይና ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ የነበረው ሊ ታይ፤ የጨዋታ ውጤት እንዲጭበረበር በማድረግ ጉቦ መቀበሉን አምኖ ነበር።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ለሻንዶንግ ታይሻን የተጫወተው ደቡብ ኮሪያዊው ጁን-ሆ በሙስና ወንጀል በቁጥጥር ሥር ይገኛል ቢልም የኮሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጫዋቹ መለቀቁን አሳውቋል።
ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ቻይናን የእግር ኳስ ማዕከል ለማድረግ ያላቸውን ሕልም ሲገልጹ አገራቸው ለዓለም ዋንጫ እንድታልፍ፣ አንድ ቀን ውድድሩን እንድታዘጋጅ ከተቻለ ደግሞ እንድታሸንፍ ያላቸውን ምኞት ተናግረው ነበር።
ባለፈው አስር ዓመት የቻይና ክለቦች ትላልቅ ተጫዋቾችን ወደ ቻይና ሱፐር ሊግ ለመሳብ በሚል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ሲከፍሉ ነበር።
ብራዚላዊው ኦስካር፣ አርጀንቲናዊው ካርሎስ ቴቬዝ እና ቤልጂዬማዊው አክስል ቪትዝል ቻይና ከተጫወቱ ከዋክብት መካከል ናቸው።
ነገር ግን ክለቦቻቸው ዕዳ ውስጥ መዘፈቃቸውን ተከትሎ የቻይና እግር ኳሰ ማኅበር በ2020 የደመወዝ ጣራ ለማስቀመጥ ተገዷል።
ማኅበሩ ይህን ውሳኔወን ባሳወቀበት ወቅት ከዚህ በኋላ ታዳጊ ተጫዋቾችን ማሳደግ ላይ እንደሚሠራ፤ የሌሎች አገራት የእግር ኳስ ከዋክብትን ወደ ቻይና እንደማያስመጣ ገልጧል።