March 26, 2024 – Konjit Sitotaw 

በምዕራብ አርሲ ዶዶላ ከተማ ላይ ትላንት ማታ 3:00 አከባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ናቸው የተባሉ አንድ ካህንን ከእነቤተሰቡ እንዲሁም ካገባ ገና ሶስት ወር እንኳ ያልሞላውን ዲያቆን እና አብራው ስትኖር የነበራቸውን እህቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸው ሄደዋል ተብሏል።

ከሁለቱ ቤተሰቦች አጠቃላይ ሰባት ሰዎችን ገድለዋቸው ሄደዋል ብለዋል።

አንድ ህፃን እንደ አጋጣሚ ያለቤተሰብ ቀርታ ተርፋለች ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ለስራ ከሲዳማ ክልል የመጡ አራት ወጣቶችም ተገድለዋል ብለዋል።

አጠቃላይ 11 ሰው ሞቷል ብለዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው ከገብረክርስቶስ ቤተክርስቲያን 50ሜርቀት ላይ ነው ብለዋል። ግድያውን የፈፀሙት በቢለዋና በጥይት ነው

“አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ሰዎች ጭምር ናቸው”

ሁለት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነቤተሰቦቻቸው በትናንትናው እለት መገደላቸውን በስፍራው ካሉ ሰዎች እና በደብሩ ቀደም ብለው ካገለገሉ አንድ አባት መረጃ ይጠቁማል።

በዚህ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ያገለግሉ የነበሩ መሪጌታ ስምረት የተባሉ አባት ባለቤታቸውን እና ሁለት ልጆቻቸውን፣ እንዲሁም ዲያቆን ዳንኤል የተባለ አገልጋይ ከነባለቤቱ እና ሌላ አንድ ሰው ጋር በድምሩ ሰባት ሰው እንደተገደለ እነዚህ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

“አሁን ቀብር ተፈፅሟል፣ የጭካኔ ግድያ የተፈፀመባቸው ለዘመናት በአካባቢው ያገለገሉ ናቸው። ጥቃቱ የተፈፀመው ትናንት ምሽት ሶስት ሰአት ገደማ ነው” ያሉኝ ምንጮች ከዚህ በፊትም በጥቅምት 2012 ዓ.ም ብዙ ሰዎች ተግድለው እንደነበር አስታውሰዋል።