


በዶዶላ ክርስቲያኖች በጥይት ተደብድበው ተገደሉ
+++
(ማኅበረ ቅዱሳን፤ ማርች 26/2024፤ መጋቢት 17/2016ዓ.ም):- በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ አካላት ተገደሉ:: ግድያው የተፈፀመው መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ መሆኑንም ከአካባቢው ምእመናን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
በተፈጸመው ግድያ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አንድ መሪጌታና አንድ ዲያቆንን ጨምሮ አምስት የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ታውቋል።
በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ይታወሳል።