ነአመን ዘለቀ ፤ “ሳናጣራ አናስርም፣ “መግደል መሸነፍ ነው”፣ “አናፈናቅልም”፣ ስለመብት እኩልነት፣ ፍትህ የዜጎች ክብርና ነጻነት እየሰበከ ስልጣን ኮንሶሊዴት እስክያደርግ ትህትናን ። ፍቅርን፣ መቻቻልን፣ “መደመርን” በጭንብልነት ተጠቀመ። ብዙዎቻችንን አጭበረበረ፣ አሳሳተ። ያለፈውን ስርአት፣ በኢፍታዊነት፣ በአፋኝነት፣ በአሸባሪነት፣ በአፈና፣ በአፈናቃይነት እየጠቀሰ በመክሰስ፣ ለፍትህን፣ ለእኩልነት፣ ለነጻነትን የነበረንን ተስፋ አለመለመ። እነደ ማር በሚጣፍጡ ቃላት እየሰበከ አጭበረበረን።
ይህ ከሃዲ ነብሰ በላ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን የደም ባህር ፣ የሰቆቃ ምድር አድርጎ ከተካቸው የወያኔ መሪዎች ብሶ ቁጭ አለ። ተስፋችንን አጨለመ። በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቶ ንጽሃንን ጭምር በየአካባቢው ጨፈጨፈ። በአዋሽ አርባ በደዴሳ እስርቱ ሺዎችን ያ አጉሮ ያሰቃያል፣ ያስርባል፣ ያስጠማል፣ በበሽታ ያማቅቃል። ሽመልስ እብዲሳ በሚመራለት ገዳይ እሰገዳይ ቡድን በኮሬ ነጌኛ የኦሮሞን ገበሬ፣ ወጣት ያሳፍናል፣ ያስገድላል፡ የአዲስ አባባን ህዝብ፣ በተለይ ድሃውን ያፈናቅላል ፣ ማህበራዊ ትስስር ይንዳል፡ “በልማት” ስም የአዲስ አበባን ቅርሶችን ያወድማል።
ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ ቁም ስቅል ፣ መከራ የሚያደሱበት፣ እነዚህን እቅመ ቢስ የወያኔ ስርአት የምራጭ ምራጮች ለመገርሰስ ተደራጅቶ፣ ተናቦ መታገል ብቸኛው አማራጭ ነው ። ይህን ዘረኛና የመንፈስ ድኩማኖች፣ የግፈኞች፣ ጨካኞች ስብስብ ለማንበርከክ ትብብር ፣ አንድነት ወሳኝ ነው። መደራጀት አስፈኣጊ ነው። በአዲስ አበባ የአገዛዙን መዋቅሮች በሁሉም አይነት የትግል ስልቶች መሽርሸር አስፈላጊነው ነው። የዚህ አረመኔ ፣ ግፈኛ ፣ ዘረኛ አገዛዝ ፍጻሜ ለማፋጠን፣ በየአካባቢው መደራጀት ወሳኝ ነው። ማንኛውን ትብብር መንፈግ።
ይህን የአፈና የግፍ ስርአት የሚሸረሽሩትን፣ የሚገዘግዙት ስልቶችን በጥናት ተግባራዊ ማድረግ። ፋኖን መደገፍ፣ የፋኖን መንፈስ በአዲስ አባባ ማስፋፋት፣ ማጠናከር። የአዲስ አበባ ፋኖን መስርቶ በህቡእ መንቀሳቀስ፣ መታገል። ይህን ማድረግ ሲቻል፣ ይህ ደካማ የግፈኞችና የጋጠ ወጦች አገዛዝ የሚንበረከክበት ግዜው ሩቅ እይሆንም። ጭቆናን በፍትህ ፣ ባርነትን በነጻነት፡ መዋረድን፣ በክብር መተካት ይቻላል። አዲስ አበባን እንደ እንደ ቅኝ ገዢ፡ እንደ ባእድ ፣ ከዚያም በባሰ ጥላቻና ቂም ያላቸው የብልጽግና ካድሬዎች ምትክ ህዝብ የራሱን ወኪሎች ከራሱ፣ ከአዲስ አበባ ልጆች መካከል መርጦ የመተዳደር መብቱን ማረጋገጥ ይችላል።
እሱነቱን ስነ ልቦናውን፣ ባህሉን፣ የጋራ እሴቶቹን የሚያከብሩ፣ የዜግነት ጥቅሙን፣ መብቱን ፣ የሰብአዊነት ክብሩን ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ተወካዮቹን ራሱ ከውስጡ፡ ከመካከሉ የሚመርጥበት ስርአት ይመሰረታል። የመጀመሪያ እርምጃ ሁልም በያለበት ይደረጅ! ያደረጅ! ህዝብ ከሁሉም ይደራጅ፣ ድርጅት! ተደራጅ! ተነስ! ተነሽ ! ተነቃነቅ! ተነቃቃ! አነቃቃ! አንቀናቅ!።ነአመን ዘለቀ