March 30, 2024 – Konjit Sitotaw
ዓለም ባንክ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ በኾኑ የኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚውል የ340 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ማጽደቁን ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።
ባንኩ በቆላማ አካባቢዎች ለሚተገብረው ፕሮጀክት የሚውለው የገንዘብ ድጋፍ የተገኘው፣ የባንኩ አካል ከኾነው ዓለማቀፉ የልማት ድርጅት እንደኾነ ባንኩ ገልጧል።
የገንዘብ ድጋፉ በቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ለድርቅ ተጋላጭ የኾኑ ሦስት ሚሊዮን አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች ድርቅን ጨምሮ የተለያዩ የአየር ንብረት ለውጦችን የመቋቋም አቅማቸውን ለማጎልበትና የተፈጥሮ አደጋ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን ለማጠናከር ባንኩ ለዘረጋው ፕሮጀክት ኹለተኛ ምዕራፍ ትግበራ የሚውል ነው።