March 30, 2024 – Konjit Sitotaw
አበዳሪ አገራት ለኢትዮጵያ እስከ ቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ድረስ የሰጡትን የብድር መክፈያ እፎይታ ሊያጥፉ እንደሚችሉ ያስቀመጡት ቀነ ገደብ ዛሬ ያበቃል።
አበዳሪ አገራቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ጋር በፈረንጆች አቆጣጠር እስከ መጋቢት 31 ማለትም ነገ ዕሁድ አዲስ የብድር ስምምነት ላይ ካልደረሰ፣ ለአገሪቱ የሰጠነውን የብድር መክፈያ እፎይታ እንሰርዘዋለን በማለት ቀደም ሲል ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
የአይ ኤም ኤፍ ልዑካን መንግሥት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ማስፈጸሚያ በጠየቀው የ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ብድር ዙሪያ ከባለሥልጣናት ጋር ለመደራደር አዲስ አዲስ አበባ የገባው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ነበር።
ልዑካን ቡድኑ በአዲስ አበባ ላንድ ሳምንት እንደሚቆይ ታማኝ ምንጮች ዘግበው የነበረ ሲኾን፣ በድርድሩ የተገኘ ውጤት ይኑር ወይም አይኑር፣ መንግሥትም ኾነ ድርጅቱ እስካኹን በይፋ የገለጡት ነገር የለም።