የክብረ በዓሉ መገለጫ የሆነው ምግብ ሲዘጋጅ

ኪንና ባህል ‹‹ጊፋታ››- የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓልን ለማስመዝገብ ሰነዱ ወደ ዩኔስኮ ተላከ

ሔኖክ ያሬድ

ቀን: March 31, 2024

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ የጊፋታ በዓልን በሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ የተዘጋጀው ሰነድ ወደ ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም ዩኔስኮ መላኩ ታወቀ፡፡

‹‹ጊፋታ››- የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓልን ለማስመዝገብ ሰነዱ ወደ ዩኔስኮ ተላከ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ጊፋታ በዳንኪራ
የሰነዱ አቅራቢ አቶ አበበ ኃይሉ
የክብረ በዓሉ መገለጫ የሆነው ምግብ ሲዘጋጅ

ወላይታዎች መስከረም ወር በገባ ከ14-20 መካከል በሚውለው እሑድ ዕለት አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበት ጊፋታ፣ የታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች አነጋገር በብሔሩ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ታላቅ በዓል ነው፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የብሔሩ ማንነት መገለጫ የሆነ የአሮጌው ዓመት ማብቂያና የአዲሱ ዓመት መጀመሪያ የመሸጋገሪያ በዓል ነው፡፡

ስለ ጊፋታ በዓል የሚያወሳውንና የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ የተዘጋጀው ሰነድ ወደ ዩኔስኮ የተላከው የመጨረሻው የማረጋገጫ (ቫሊዴሽን) መድረክ ከተካሄደ በኋላ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በማኅበራዊ ገጹ እንዳስታወቀው፣ ሰነዱ ወደ ዩኔስኮ ከመላኩ በፊት የመጨረሻው የማስመረጫ ሰነድ ዝግጅትን አስመልክቶ የይሁንታ መድረኩ የተከናወነው በሶዶ ከተማ መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ነው፡፡

‹‹ጊፋታ››- የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓልን ለማስመዝገብ ሰነዱ ወደ ዩኔስኮ ተላከ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ጊፋታ በዳንኪራ
የሰነዱ አቅራቢ አቶ አበበ ኃይሉ
የክብረ በዓሉ መገለጫ የሆነው ምግብ ሲዘጋጅ

መድረኩ የተዘጋጀውም የቅርስ ባለስልጣን ከወላይታ ዞን የባህልና ቱሪዝም መምሪያ፣ ከወላይታ ዩኒቨርሲቲና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር በመቀናጀት ሲሆን፣ በመድረኩ ለማኅበረሰቡና ለአመራሩ ሰነዱን ያቀረቡት የፎክሎር ባለሙያው አቶ አበበ ኃይሉ ናቸው፡፡

ጊፋታ ሲገለጽ

ወላይታዎች የአዲስ ዘመን ብሥራትን ‹‹ጊፋታ›› በማለት ይጠሩታል፡፡

ጊፋታ/ ግፋታ ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን፣ ብሔረሰቡ አዲስ ዓመትን አንድ ብሎ የሚጀምርበት የአዲስ ዓመት መግቢያ ብቻም ሳይሆን የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ነው፡፡

‹‹ዮዮ ጊፋታ›› የወላይታ ባህል አዋቂዎችና ጥበበኞች የጨረቃን ዑደት ስሌት መሠረት በማድረግ፣ ማኅበረሰቡ ከክረምት ወደ ብራ፣ ከጭጋጋማ ድባብ ወደ ብርሃናማ ዓውድ፣ ከአሮጌ ዓመት ወደ አዲስ ዓመት የሚደረገውን ሽግግር የሚያበስሩበት ነው፡፡ የአዲስ ዓመት ዕቅዳቸውና ጥረታቸው እንዲሳካ አምላክን የሚማፀኑበት የተስፋና የተምሳሌት በመሆኑ ጊፋታ በየዓመቱ ይከበራል፡፡  

የወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ እትም ላይ እንደሰፈረው፣ ጊፋታ ማለት ባይራ (ታላቅ)፣ መጀመሪያ እንደ ማለት ሲሆን በሌላ በኩል ጊፋታ ማለት መሻገር ማለት ነው፡፡ ይህም ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውን ይገልጻል፡፡ ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡

አቶ መሐመድ ሀምቢሶ ‹‹ውበት›› በተሰኘው የደቡብ ባህልና ቱሪዝም ድርሳን ላይ እንደጻፉት፣ ጊፋታ ነጭ ልብስ ለብሶ በጋዜ (በኩር ጨዋታ) በጋራ ሆኖ በመጫወት የሚከበር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ ነው፡፡በሌላ በኩል፣ ወላይታ በኩር ሆኖ የተወለደ ልጅ ወንድ ከሆነ፣ ‹‹ግፋቶ›› ሴት ከሆነች‹ ‹‹ግፋቴ›› ብሎ ይጠራል፡፡ ግፋታ ማለት መሻገር ማለት ሲሆን ከዓመት ወደ ዓመት፣ ከጥላቻ ወደ ዕርቅ፣ ከመጥፎ ሥራ ወደ ጥሩ ሥራ መሻገርን የሚያመላክት ቃል ነው፡፡

መስከረም ወር በገባ ከ14-20 መካከል በሚውለው እሑድ ዕለት አዲሱን ዓመት ይቀበሉታል፡፡ በዓሉ የሚውልበት እሑድ ስሙም ‹‹ሹሃ ወጋ›› የእርድ እሑድ ይባላል፡፡

ቃየ አሹዋ (ቃንጡዋ) ቁርጥ ከበሬው ሥጋ ምርጥ የሆነው ክፍል ተቆርጦ በቅቤ በተለወሰ ዳጣ በርበሬ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ነው፡፡ ይህንን ቤተሰብ በአንድ ቦታ በመሰብሰብ ኤርጊያ የሚባል የእንሰት ቅጠል በማንጠፍ ቁርጡን በሥጋ በቅጠሉ በመዘርገፍ ዙሪያውን ከበው በመቀመጥ በዳጣ በርበሬ እያጠቀሱና እርስ በርስ እየተጎራረሱ የሚመገቡት ምግብ ነው፡፡

እንደ አቶ መሐመድ አገላለጽ፣ በወላይታ የበሬ ድለባ ሥርዓት በጣም የተለየ ሆኖ በሬ በሰው ትንፋሽ እየተጋራ ‹‹ጢሁዋ ሆምቢያ›› በሚባለው በተከደነ አጥር ውስጥ የተለያዩ የእህል ዝርያዎችን እየተመገበ ስለሚቀለብ ቁርጥ ሥጋው የተለየ ጣዕም አለው፡፡ በዚህ ምክንያት ወላይታ በጥሬ ሥጋ ቱሪዝም ትታወቃለች፡፡

የግፋታ በዓል ባህላዊ ምግብ ዝግጅት በከፊል ቃየ አሹዋ (ቃንጡዋ) ቁርጥ ከበሬው ሥጋ ምርጥ የሆነው ክፍል ተቆርጦ በቅቤ በተለወሰ ዳጣ በርበሬ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ነው፡፡ ይህንን ቤተሰብ በአንድ ቦታ በመሰብሰብ ኤርጊያ የሚባል የእንሰት ቅጠል በማንጠፍ ቁርጡን በሥጋ በቅጠሉ በመዘርገፍ ዙሪያውን ከበው በመቀመጥ በዳጣ በርበሬ እያጠቀሱና እርስ በርስ እየተጎራረሱ የሚመገቡት ምግብ ነው፡፡

በወላይታ የበሬ ድለባ ሥርዓት በጣም የተለየ ሆኖ በሬ በሰው ትንፋሽ እየተጋራ ‹‹ጢሁዋ ሆምቢያ›› በሚባለው በተከደነ አጥር ውስጥ የተለያዩ የእህል ዝርያዎችን እየተመገበ ስለሚቀለብ ቁርጥ ሥጋው የተለየ ጣዕም አለው፡፡ በዚህ ምክንያት ወላይታ በጥሬ ሥጋ ቱሪዝም ትታወቃለች፡፡

ጥጣ (ጥብስ) ለጥብስ የሚሆነውን ሥጋ ዘልዝለው አግድም በተዘረጋው ትልቅ እንጨት በማንጠልጠልና እሳት በማንደድ ሲጠበስ ቻቻቻቻ…. የሚል ድምፅ እያሰማ የጮማው ብዛት እሳት እያነደደ የበሰለውን ሥጋ ከእሳት አውጥተው የሚመገቡት የምግብ ዓይነት ነው፡፡

እንደ ጥናታዊው ጽሑፍ የበዓሉ ዝግጅት የሚጀመረው በወርኃ ሐምሌ በሚደረገው የጉልያ ስርዓት ሲሆን አባቶች ያላቸው ድርሻ ለልጆቻቸው አዳዲስ ልብሶችን መግዛት ዋነኛ ተግባር ነው፡፡ ለጊፋታ በዓል መቀበያ)ከሚዘጋጁት ምግቦች አንዱ ‹‹ጉርዱዋ›› የተባለውን ምግብ ለማዘጋጀት በበልግ ጊዜ ገብስ ይዘራል፡፡ ገብሱን በማጨድና በመሸክሸክ ለሚስቶቻቸው ያቀርባሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ወንዶች ለአስራ አምስት ቀን የሚሆን የማገዶ እንጨት በጊዜ ፈልጠው ያከማቻሉ፡፡ ለከብቶችም የሚበቃ ሣር በበቂ ደረጃ ተዘጋጅተው ከነማባያው ቦሌ (አዱዋ) ይቀርባል፡፡ ለተለያዩ ቅመማ ቅመሞች ግዥ ለሚስቶቻቸው በቂ ገንዘብ ይሰጣል፡፡ በወንዶች ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ ለበዓሉ ዝግጅት የሚያስፈልገውን ሥጋ ወደ ቤት ለማምጣት ለአስራ አንድ ወራት የሚያስቀምጡት ተቀማጭ ገንዘብም የወንዶች ድርሻ ነው፡፡

ሴቶች ለቆጮ የሚሆን እንሰትን በጊዜ ይፍቃሉ፡፡ ከእንሰት ፍቅፋቂ ቡልአ ይወጣል፤ ከቡልአው ሙቿ የተባለው የቡልአ ፍርፍር እንዲዘጋጅ ያደርጋሉ፡፡ ከቆጮው ባጭራ የተባለው የሆድ መፍታቻ ምግብ ለበዓሉ ዋዜማ ይዘጋጃሉ፡፡ የተለያዩ ማባያ የወላይታ ዳታ በርበሬ ይዘጋጃሉ፡፡ የተለያዩ መጠጦች ቦርዴ፣ ጠጅ፣ ጠላ እና ወተት በትልቅ ጋንና እንስራ ይዘጋጃሉ፡፡

የቅቤ ዕቁብንም በመጣል ሴቶች ብዙ ቅቤ ያጠራቅማሉ፡፡ ለልጆች ስጦታ መስጫ ሎሚ ተገዝተው በእንስራ ያጠራቅማሉ፡፡ ለቂጣ የሚሆን የቦቆሎና የማሽላ ዱቄትም ያዘጋጃሉ፡፡

የግፋታ በዓል እየተቃረበ ሲመጣ በተከታታይ ያሉት የሦስት ሳምንታት ስያሜያቸው ሃሬ ሃይቆ፣ ቦቦዳ እና ጎሻ ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሃሬ ሃይቆ የሚባለው የጳጉሜን ወር ሲሆን አህያ ለሽያጭም ሆነ ለበዓል ዝግጅት የሚሆን ዕቃ ከቤት ወደ ገበያ ጭና የምትወስድበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡ ከገበያ መልስም ለቤቱ የሚያስፈልገውን ዕቃ ጭና ትመጣለች፡፡ ይህ በቀን ሁለቴ የሚጫንበት ዕረፍት የማይሰጥ አህያ ፈጅ ሳምንት ይባላል፡፡

ከመስከረም 1-7 ያለው ሳምንት ቦቦዳ ይባላል፡፡ ሆድ ሞርሙር ማለት ነው፡፡ ቤተሰብ በዓሉን ለማዘጋጀትና በደስታ ለማሳለፍ በእጃችን ምን አለ?፣ ምን ጎደለብን? በማለት በሥጋት የሚያሳልፉበት ሳምንት ነው፡፡ ሦስተኛው ሳምንት ደግሞ ጎሻ ሲባል ትርጓሜውም ‹‹የዕብደት ሳምንት›› እንደማለት ነው፡፡ ሳምንቱ የዕብደት ሳምንት ተብሎ የሚጠራበት ዋናው ምክንያቱም ለበዓሉ የጎደለውን ነገር በፍጥነት ለማሟላት ምርጫ የማይሰጥ ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡

የጎሻ ሳምንት እያለቀ ሲመጣ ሐሙስ ዕለት ‹‹ኮሴታ ሐሙሳ›› ይባላል፡፡ ትርጓሜውም የእንኩሮ ሐሙስ ማለት ነው፡፡ ለቦርዴውና ጤላ እንኩሮ የሚነኮርበት ቀን መሆኑ ነው፡፡ ዓርብ ደግሞ ‹‹ሱልአ አርባ›› ይባላል፡፡ በየቤቱ ለቦርዴው የሚዘጋጀው ዱቄት የሚቀቀልበት ቀን ማለት ነው፡፡ ቅዳሜ ባጭራ ቄራ ይባላል፡፡ ቀኑ የሆድ ማፍታቻ ወይም ማለስለሻ ምግብ የሚዘጋጅበት ቀን ነው፡፡ በእለቱ የሚበሉ ምግቦች ባጭራ፣ ጉርዷ፣ ሙቿ ወዘተ ናቸው፡፡ የሚቀጥለው ቀን ሹሃ ወጋ ይባላል፡፡ የእርድ እሁድ መሆኑ ነው፡፡

 እሑድ የአዲስ ቀን ብሥራትም ነው፡፡ የአዲሱ ዓመት 2ኛ ቀን ‹‹ታማ ሰኞ›› ይባላል፡፡ የእሳት ሰኞ መባሉ ነው፡፡ በዚህ ቀን አንዱ ከአንዱ ቤት እሳት መዋዋስና መቀባበል አይቻልም፡፡ በዓመት አንድ ቀን ወላይታዎች በራሳቸው ቤት እሳት እያነደዱ የሚውሉበት ቀን ነው፡፡

የአዲሱ ዓመት ከገባ 3ኛ ቀኑ ማክሰኞ ‹‹ጪሻ ማክሰኞ›› ይባላል፡፡ ዘመድ ለዘመድ አደይ አበባ እና ኮርማ ጪሻ የተባሉ አበባዎችን ይዘው እንኳን አደረሳችሁ እያሉ የአዲስ ዓመት ብሥራት የሚገልጽበት ቀን ነው፡፡

የአዲስ ዓመት 4ኛ ቀን ረቡዕ ‹‹ጋዜ ኦሩዋ›› ሲባል በዚህ ቀን የሰፈሩ ወጣቶች በየመንደሩ በታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ደጅ ተሰባስበው የግፋታ በዓል ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ጋዜ በጋራ ሆነው ‹‹ሀያያ ሌኬ ›› እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው የሚጫወቱበትና ልጃገረዶችን ሎሚ በመለመን የሚፈልጓትን የሚመርጡበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ልጃገረዶች አንድ ላይ ሆነው በየቡድን ቁጭ ብለው ወንዴና ሴቴን ከበሮ እየመቱ ‹‹ወላወላሎሜ›› እያሉ የሚመርጡትን ወንድ ሎሚ በመስጠት የሚመርጡበት፣ እንዲሁም ሴቶች ለሚዜነትና ለጓደኝነት ከመረጧት ሴት ጋር በጥርስ አንድ ሎሚን ለሁለት የሚከፋፈሉበትና ስማቸውን ሲጠራሩ ‹‹ሎሜ ሎሜ›› የሚባባሉበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ዕለት ጋዜ አሩዋ ነው፡፡

የጋዜ ጨዋታ ለሳምንታት ከደመቀበት እየቀዘቀዘ ይሄዳል፡፡ ከዚያ ‹‹ጊፋታ›› እስኪሸኝ ድረስ በየቤቱ ሁሉም ሰው ወንዴንና ሴቴን ከበሮ ለልጆች ገዝተው በየሰፈሩ ቤት ምግብ እየተበላና መጠጥ እየተጠጣ ይዘፈናል ይጨፈራል፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡