ደቡባዊ ሌባኖስ

ከ 6 ሰአት በፊት

በደቡባዊ ሊባኖስ በተፈጸመ ጥቃት ለሥራ የተንቀሳቀሱ ሦስት የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች እና አስተርጓሚያቸው ጉዳት ደረሰባቸው።

የሊባኖስ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ጉዳት የደረሰባቸው የእስራኤል የድሮን ጥቃት በፈጠረው ፍንዳታ ነው ሲል ዘግቧል።

እስራኤል ግን ጥቃቱን እኔ አልፈጸምኩም ብላለች።

የተባበሩት መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸው ሠራተኞቹ የሕክምና እርዳታ እያገኙ መሆኑን እና የፍንዳታውን ምንጭ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

ፍንዳታው ያጋጠመው የተመድ ሠራተኞች በእስራኤል እና ሊባኖስ ድንበር ላይ በእግር እየተጓዙ የቅኝት ስራ እየሰሩ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይሎቹን ዒላማ ማድረግ “ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው” ብሏል።

የመንግሥታቱ ቃል አቀባይ አንድሪያ ቴኔንቲ እስራኤል በሊባኖስ የሚገኙ መገኘኛዎችን መምታት መቀጠሏ በቀጠናው ሰፊ ግጭት እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ጉዳት ስለደረሳበቸው ግለሰቦች ዜግነትም ሆነ አሁን ስላሉበት ሁኔታ ተመድ ያለው ነገር የለም።

የሊባኖስ የዜና ወኪል የተመድ ሠራተኞች የነበረቡበትን የድንበር አካባቢ “የጠላት ድሮኖች”

ወርረው ነበር ብሏል።

እስራኤል ባወጣችው ማስተባበያ የአገሪቱ ጦር የተመድ ሠራተኞችን የያዘውን ተሸከርካሪ ዒላማ አላደረገም ብሏል።

ሐማስ መስከረም 26 እስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላ አሁን ላይ በየቀኑ ሊባል

በሚችል መጠን እስራኤል እና ሔዝቦላ በዚህ የድንበር አካባቢ የተኩስ ልውውጥ ያደረጋሉ።

መቀመጫውን ሊባኖስ ያደረገው የሺያ ሙስሊም የሚሊሻ ቡድን በኢራን እየተደገፈ ለሐማስ

አጋርነቱን ለማሳያት ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ያስወነጭፋል።

ከትናንት በስቲያ አርብ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት የሔዝቦላን ጥቃት

ከመከላከል አልፈን ቡድኑን ማጥቃት እንጀምራለን ብለው ነበር።

“የትም ይደበቁ እናገኛቸዋለን” ሲሉ ተናግረው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካ በራፋህ ላይ የሚደረግ መጠነ ሰፊ ጥቃት አልደግፍም ማለቷ

እስራኤል ላይ ጫናን ፈጥሯል።

እስራኤል ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በሚገኙበት ራፋህ የምድር ኃይል ዘመቻ ለማድረግ

በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

የጆ ባይደን አስተዳደር በጋዛ የሰላማዊ ሰዎች ሞት መብዛት እና የሰብዓዊ እርዳታ ቀውስ

አስቦባኛል በማለት ለእስራኤል ያሳይ የነበረውን አጋርነት እያላላ መጥቷል።