![ትራምፕ [ግራ] ባይደን [ቀኝ]](https://i0.wp.com/ichef.bbci.co.uk/ace/ws/640/cpsprodpb/e1f1/live/8f8e8210-ef1f-11ee-b0e1-b9dd5ac46984.jpg?w=800&ssl=1)
ከ 6 ሰአት በፊት
የጆ ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ቡደን ዶናልድ ትራምፕ በማሕበራዊ ሚድያ ገፃቸው የለጠፉትን ቪድዮ ተከትሎ ትችት እየሰነዘሩ ነው።
ትራምፕ ያጋሩት ቪድዮ ፕሬዝደንት ባይደን እጅና እግራቸው ተጠፍሮ የጭነት መኪና ላይ ተጭነው ያሳያል።
ትራምፕ ከመጪው ኅዳር ምርጫ በፊት “በተደጋጋሚ ፖለቲካዊ አመፅ ለማስነሳት እየሞከሩ ነው” የሚል ትችት ደርሶባቸዋል።
የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡደን ቃል አቀባይ በበኩላቸው ዲሞክራቶች ትራምፕ ላይ “አመፅ ሲጠሩ ነው የቆዩት” ብለዋል።
ትራምፕ አርብ ዕለት ነው ቪድዮውን ትሩዝ በተሰኘው ማሕበራዊ ሚደያቸው ላይ የለጠፉት።
ከቪድዮው ጋር አያይዘው የለቀቁት መልዕክት እንደሚያሳየው ቪድዮው የተቀረፀው ኒው ዮርክ ግዛት ሎንግ አይላንድ አቅራቢያ ነው።
ትራምፕ፤ አንድ የፖሊስ መኮንን ሥራ ላይ እያለ መገደሉን ተከትሎ ሐሙስ የተዘጋጀውን ዝክር ታድመው ነበር።
ቪድዮው ላይ እንደሚታየው ሁለት በአሜሪካ ባንዲራ ቀለም ያሸበረቁ መኪናቸዎች ለፖሊስ ያላቸውን ደጋፈ የሚያሳይ ፅሑፍ ለጥፈዋል።
- እነ አቶ ክርስቲያን ታደለ “እንደ መደበኛ ታሳሪ እንዲታዩ” ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላለፈ29 መጋቢት 2024
- ቤልጂም ውስጥ የተገኙት ተሰምቶ የማያውቀው የማርቪን ጌይ ሙዚቃ እና ንብረቶቹከ 6 ሰአት በፊት
- ሶማሊያ ዜጎቿን በሞት የምትቀጣበት የባሕር ዳርቻው የእግር ኳስ ሜዳከ 6 ሰአት በፊት
ከሁለቱ መኪናዎች መካከል አንዱ “ትራምፕ 2024” የሚል ፅሑፍ ያለበት ሲሆን የመኪናው የኋላኛው ክፍል ፕሬዝደንት ባይደን እጅና እግራቸው ወደኋላ ተጠፍሮ ይታይበታል።
የቀድሞው ፕሬዝደንት ለምርጫ ቅስቀሳ ብለው ይህ ምስል ያለበት ቪድዮ ማጋራታቸው ወቀሳ እንዲዘንብባቸው ምክንያት ሆኗል።
“ትራምፕ በተደጋጋሚ ግጭት ሲቀሰቅሱ ቆይተዋል። ሰዎች ይህን ጉዳይ በቁም ነገር የሚመለከቱበት ጊዜ አሁን ነው” ሲሉ የባይደን ምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቲቨን ቼውንግ በበኩላቸው “ዲሞክራቶች እና ያበዱ ደጋፊዎቻቸው ትራምፕ ላይ አመፅ ከመጥራት ባለፈ የፍትሕ ሥርዓቱን መሣሪያ አድርገው እየተጠቀሙ ነው” ብለዋል።
ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩት ትራምፕ አራት የተለያዩ ክሶች ቀርበውባቸዋል። አንዱ ምርጫን ሌላኛው ደግሞ ገንዘብ ማጭበርበርን በተለመከተ የተከሰሱበት ክስ ከኅዳር በፊት ችሎት ፊት እንዲቆሙ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ግምት አለ።
ትራምፕ በሁሉም ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ አስተባብለዋል። የቀረበብኝ ክስ ፖለቲካዊ ነውም ይላሉ።
ሁለቱ ዕጩዎች ምርጫው ከመቃረቡ በፊት በተለያዩ መንገዶች እየተወቃቀሱ ይገኛሉ።
በያዝነው የአውሮፓውያኑ ወር መባቻ ኦሃዮ የተሰኘው ግዛት ተገኝተው ካልተመረጥኩ “ደም መፋሰስ” ይሆናል ያሉት ትራምፕ ከፍተኛ ትችት አስተናግደዋል።
ባይደን ይህን በተለመከተ ምንም ባይሉም ትራምፕ ግን የባይደን ቡድን እና ሚደያው ንግግሬን ከአውድ ውጭ ወስዶብኛል ሲሉ ወቅሰዋል።