March 31, 2024 

( ነዐመን ዘለቀ )   =  ሪፖርተር ያወጣውን ዘገባ አንብቡት፣ ነውረኛው አጭበርባሪ የበሻሻ ደላላ፡ “ማንም ጭቃ ያቦካውን” የሚላቸው፣ በአዲስ አበባ በቅርስነት የተመዘገቡ በርካታ ታሪካዊ ግንባታዎች እያፈረሰ መሆኑ ይበልጥኑ ግልጽ ያደርጋል። https://thereporterethiopia.com/39408/

በአዲስ አበባ አብይ እህመድ አያፈረሰ የሚገኘው የከተማው ቅርሶች ወይንስ እሱ እንደሚለው “ማንም ያቦካው ጭቃ”? ከመለስ ዘናዊ የባሰ ጊዜ ይመጣል ብዬ በህልሜም አስቤ አላውቅም ነበር። ለቀድሞው ጠ/ሚ ከነበረኝ መጸየፍ የተነሳ ደሜ ሳይፈላ 5 ደቂቃ ማየት እልችልም ነበር።

የዚህ ነውረኛ ፣ አጭበርባሪ ብሶ ቁጭ እለ። የአብይ አህመድ ብልግና፣ ትቢኢት፣እብሪት፣ ለህዝብ ያለውን ንቀት ተደጋጋሚ ውሽትና ማጭበርበር በየግዜው ማየትና መስማት የሚዘገንን ነገር የለም። የህዝብን የማሰብ ፣ የማስታወስ አቅም በየጊዜው ይሰድባል። የሌለውን አለ፣ ያሆንውን ሆነ፣ ትላንት የተናገረውን በሳምንቱ መገልበጥ። በእሱ የበሻሻ አራዳ ጭንቅላት ያለው እሳቤ ግልጽ ነው። በአብይ እህመድ የቅዠት አለም ህዝብ “ሾርት ሚሞሪያም ነው” ።

እሱ ደግሞ ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን አድራጊ፣ 7ኛ ንጉስ ነው። በአዲስ አበባ ከቅርብ አመታት በፊት የተጀመረውን ነዋሪውን ማፈናቀል፣ ቅርሶችን ማፍረስ ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ለማሳየት በቀደም እለት የተጠቀመበትን ቃል እስቲ እንመዝነው “ ማንም ያቦካውን ጭቃ ታሪካዊ ቅርስ አይደልም” በማለት ሊያሳምን ነው የሞከረው። በእርግጥ ኢፍትሃዊነት ፣ ጋጠ ወጥ በሆኑ በርክታ ኩነቶች የፈረሱት ጭቃ ቤቶች ብቻ ናቸው? እሱ እንደሚለው? እንዲሁም ማንም የማይቆምላቸው ድሃ የከተማው ነዋሪ ተፈናቃዮች “የጭቃ ቤቶች ብቻ” ናቸው የፈረሱት? ለአዲስ አበባ ቅርስ መሆናቸው የታወቀ፣ የተመዘገቡ ታሪካዊ እሴት ያላቸው “ቅርስ” ስለመሆናቸው የታተመባቸው እንዲፈሱ አልተድረገም? ሃቁ ግልጽ ነው። ማስረጃዎች አሉ።

የአብይ አህመድ በሰጠው ትእዛዝ በርክታ በቅርስነት የተመዘገቡ ግንባታዎች እንዲፈሱ ተደርገዋል። ስውየው ግን ለህዝብ ካለው ንቀት፣ ማጭበርበር፣ ሃስት መደራረት ለከት የለውም። እንደሚታወቀው ታሪካዊ ቅርሶች መመዝገብ፣ ለህዝብም፣ ለሀገርም፣ ለከትሞችም ያላቸውን ፋይዳ የሚመርመር የራሱ እውቀት መመዘኛ አላቸው። የራሱ ማእቀፍ፣ ይራሱ አሰራር አለው። በሰለጠነው አለም ሀገራዊ ቅርሶች አሉ፣ የክፍለ ሀገር ቅርሶች አሉ፣ የከተማ ቅርሶችም አሉ፣ ለምሳሌ በዚህ በአሜካን ሀገር በቨርጂኒያ ግዛት ፣ ኦልድ ታውን/Old Town በሚባል አካባቢ የዛሬ 200 ፣ 100 አመት የተገነቡ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ፋይዳና እሴት የሚያወሱ ቅርሶች በቅርስነት ተይዘው፣ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ተጠብቀው ቆይተዋል።

እንዳንዶቹም ለቱሪዝምና ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ውለዋል፣ እነዚህ ቅርሶች ሀገራዊ እይደሉም ከአሚሪካ ፣ ከእንግሊዝ፣ ከቻይና ሀገራዊ ቅርሶች ጋር እይመደቡም፣። በተመሳሳይም በአዲስ አባባ የሚገኙ በቅርስነት የተመደቡ፣ ቅርስ ስለመሆናቸው የተመዘገቡ ቅርሶች ለአዲስ አበባ ከተማ ፣ ለነዋሪዎቿ የጋራ ማንነት፣ የኋላ ታሪክ ፋይዳ አላቸው፣ የከተማው ቅርስ ታሪካዊ ፋይዳና እሴታቸው የከተማዋ ነው። ከቅድመ እያት፣ እያት፣ አባት እናት ጀሞር በከተማዋ የኖሩ ዜጎች የጋራ እሴቶች ናቸው። የግድ ከአክሱም ከላሊበላ ፣ ከፋሲለደስ ቤተ መንግስት ጋር መመደብና መነጻጸር እይጠበቅባቸውም።

ከአለፈው አመት ጀምሮ እየፈረሱ የሚገኙ ግንባታዎች፣ “የከተማ ቅርስ” መሆናቸውን ሞያዊ ብይን ተስጥቶባቸው በህንጻዎቹም። ግንባታዎቹም ላይ “ቅርስ” ስለመሆናቸው ታትሞባቸዋል። እነዚህ ቅርሶች ጭምር እያፈረሰ የሚገኘው የአብይ አህመድ፣ የሽመልስ አብዲሳ፣ የአዳነች አቤቤ አገዛዝ እይኑን በጨው ታጥቦ ነው እንግዴህ “ማንም ያቦካውን ጭቃ” በሚል ወንጀሉን፣ ጋጠ ወጥነቱን፣ ህገ ወጥነቱን፣ ኢፍትሃዊነቱን፣ እብሪቱን፣ ማን እለብኝነቱን ለመሸፋፈን የሚጋጋጥጠው። ሰውየው ግን ምንም ለከት የሌላው ነውረኝነት፡ አጭበርባሪነት፣ ከሃዲነት ለከት የለውም የምንለውም ለዚህ ነው። በእነዚህ ደንቆሮዎች እሳቤ ደግሞ ይሄ ፓለቲካ መሆኑ ነው። መርህ የለም፣ እሴት/ቫሉ የለም። የምትፈልገውን ለማሳካት ምንም ከማንም፣ በየትም እድርሀ ማገኘት ነው ግቡ፣ ስልቱም የእብይ እህመድ ሌላው ጥንድ/ ክፉ ፓሊስ ሆኖ በመልካም ፓሊስ ክፉ ፓሊስ ጨዋታ የክፉ ፓሊስ ሚና የሚጫወተው የአብይ አህመድ ገዳይ አስገዳይ ድብቅ መንግስት/ኮሬ ነጌኛ ሊቀ መንበር ሽመስል አብዲሳ እንደነገረን “ኮቪንስና ኮንፉስ” በማድረግ ነው።

የማይገናኘውን በማገኛነት ፣ የማይወዳደረውን በማወዳደር፣ እዚህ እንድ ነገር፣ እዚያ ጋር የተቃራኒውን በመናገር ግቡን ማሳካት ኢላማው ያደረገ ፣ ግርድፍ ያማክያቪላዊ ስልት። የሚተቹትን፣ ሃቁን የሚያገሩንት በመዝለፍና በማስጨብጨብ በድንጋይ ማምረቻ የተመረቱ የብልጽግና ግኡዛን ባለስልጣኖች፣ እንዲሁም ውዳቂ ካድሬዎቻቸው ማስገልፈጥ፣ ማስጨብጨብ፣ ለምዶበታል። ስለዚህም ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ብሎም የአለም ህዝብ ሁሉ ለማታለል፣ ለማጭበርበር፣ ከነባሪዊው ሁኔታና ከሃቁ በተቃራኑ ለማሳመን የሚችል ይመስለዋል። የራሱን ወንጀል፣ መክሸፍ፣ ውሸት፣ ኢ-ፍታዊነት ፣ ነውረኛ እርምጃዎች “ትክክል” መሆኑን ለማሳመን፣ ምንም ከማለት እንደማይመለስ በተደጋጋሚ አሳይቶአል። ነጩን ጥቁር፣ በሬ ወለደ ከመቀባጠር፣ የማይገናኙ፣ ከነበራዊ ሁኔታው ያፈነገጡ፣ ሃቅ ያልሆኑ ነገሮች አይኑን በጨው ታጥቦ ከመዋሸት ያማይመልስ ለከት የለሽ ወራዳ። ( ነዐመን ዘለቀ )