March 31, 2024 

“ ከተጎጂዎች መካከል 30,427 ህፃናት ናቸው። የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል ” – ሴቭ ዘ ቺልድረን

በሶማሌ ክልል ከተከሰተ የወራት ያለፈው የጎርፍ አደጋ የውሃ መጠኑ እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም ትንበያዎች የሚያመለክቱት በመጪው የዝናብ ወቅት ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንዲሚችል ስለሆነ፣ ህብረተሰቡም አሁንም ካለፈው የጎርፍ አደጋ ገና እያገገመ በመሆኑ፣ ትልቅ ፈተናና ስጋት መፍጠሩን በቦታው የሚገኘው የህፃና አድን አድን ድርጅት (Save the children) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የድርጅቱ ሶማሌ ክልል ምሥራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አህመድ ምን አሉ ?

– “ ጎርፉ ከቀነሰ በኋላ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። በሚመለሱ ጊዜ ግን ቤታቸውን ለመጠገን፣ እንደገና ለመገንባት፣ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ድጋፍ ይፈልጋሉ። ሆኖም ይህ ድጋፍ በሚፈለገው መጠን አልተሰጠም። ”

– “ በክልሉ በጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደርሷል። ” (ከወራት በፊት የሟቾች ቁጥር 23 እንደነበር ይታወሳል)

– “ አደጋው በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አፈናቅሏል። በሶማሌ ክልል ብቻ ከ1,000,000 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል። 400,000 የሚሆኑ ተፈናቅለዋል። ”

– “ በተለይ የሸበሌ ዞን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን፣ በዞኑ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ከሞላ ጎደል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ”

– “ በጎርፍ አደጋው ላይ በተደረገው የጋራ ዳሰሳ ፦ 84, 800 አባውራዎች (490, 000 ሰዎች) ተጎድተዋል። ከእነዚህም መካከል 34, 441 የሚሆኑ አባውራዎች (206, 646 ሰዎች) በሸበሌ ዞን በሚገኙ 8 ወረዳዎች ተፈናቅለዋል። ከተጎጂዎች መካከል 49, 430 ሴቶች፣ 30, 427 ህጻናት እና 25, 253 አረጋውያን ናቸው። ”

– “ ከብቶች በጎርፍ አደጋው በጣም ተጎድተዋል፣ እንደሚታወቀው ለበርካታ ተጎጂ ማህበረሰቦች ወሳኝ የገቢ ምንጭ ናቸው። በጎርፉ አደጋው ከ19, 822 በላይ እንስሳት ሞተዋል። መተዳደሪያቸው የነበረ ከ94,000 ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰብልም ወድሟል። በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ሙሉና በከፊል ወድመዋል። ”

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-03-31