
ከ 4 ሰአት በፊት
ለዘገባ ሥራ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አውሮፕላን ላይ የሚሳፈሩ ጋዜጠኞች ከአውሮፕላኑ ላይ ‘ማስታወሻ’ በሚል ዕቃ መስረቅ እንዲያቆሙ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው።
በቅርቡ ፕሬዝዳንት ባይደን ለሥራ ወደ ምዕራባዊ የአገሪቱ ክፍል በኤር ፎርስ ዋን ከበረሩ በኋላ በአውሮፕላኑ ላይ የንብረት ቆጠራ ከተካሄደ በኋላ ብዙ ንብረት ጎድሎ ተገኝቷል።
በቆጠራው ወቅት የፕሬዝዳንቱ አርማ ያለባቸው በወርቅ ቀለም ያሸበረቁ ሳህኖች እና የትራስ ጨርቆች ጎድለው ተገኝተዋል።
የዋይት ሃውስ የጋዜጠኞች ማሕበር ከአውሮፕላን ዕቃዎችን ይዞ መውረድ የተከለከለ ነው ብሏል።
ባለፈው ሳምንት ማሕበሩ ለጋዜጠኞች በላከው የኢሜይል መልዕክት ይህ ተግባር ከፕሬዝዳንቱ ጋር የሚጓዙ ጋዜጠኞችን ስምን የሚያጎድፍ በመሆኑ በአስቸኳይ መቆም አለበት ብሏል።
አልፎ አልፎ ጋዜጠኞች ከፕሬዝዳንቱ ጋር ለዘገባ ሥራ ሲጓዙ የፕሬዝዳንቱ ዓርማ ያረፈበት ኤም&ኤምስ ቸኮሌት እንደ ማስታወሻ ይሰጣቸዋል።
ይሁን እንጂ ጋዜጠኞች የኤር ፎርስ ዋን አርማ ያለባቸውን እንደ ማንኪያ፣ ሹካ እና ፎጣ የመሳሰሉ ቁሶችን ያለፍቃድ መውሰዳቸውን የተለመደ ተግባር አድርገውት ቆይተዋል።
- አጀማመሩ በትክክል የማይታወቀው የ‘ኤፕሪል ዘ ፉልስ’ ታሪክከ 5 ሰአት በፊት
- ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን በአካባቢ ምርጫ ያልተጠበቀ ሽንፈት አጋጠማቸውከ 5 ሰአት በፊት
- ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን አስታወቀች31 መጋቢት 2024
የአሜሪካ ድምጽ የዋይት ሃውስ ዘጋቢ የሆነው ሚሻ ኮማዶቪስኪይ ከፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን ላይ በርካታ ዕቃዎችን መውሰዱን ያምናል።
“እነዚንህ ዕቃዎች የሰበሰብኩት ሕግ ተላልፌ አይደለም። ማንንም ለማሸማቀቅ ያደረጉት አይደለም” በማለት ከፕሬዝዳንቱ አውሮፕላን ከወሰዳቸው ዕቃዎች መካከል አንዱ የሆነው የኤር ፎርስ ዋን አርማ ያለበትን ከወረቀት የተሰራ መጠጫ ያሳያል።
ጋዜጠኛው የባይደን ፊርማ ያረፈበት ኤም&ኤምስ ቸኮሌት እንዳለውም ያሳያል።
“በሰማይ ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢሮ” ተብሎ የሚገለጸው ኤር ፎርስ ዋን አውሮፕላን በሦስት ወለሎች የተከፋፈለ ሲሆን 372 ሜትር ስኩዌር ስፋት አለው።

ይህ ቦይንግ 747-200ቢ አውሮፕላን የተሠራበት መንግድ እና የተገጠሙለት መሳሪያዎች በጦር አውሮፕላን ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት ያደርገዋል።
አውሮፕላኑ ከአየር ላይ ጥቃቶች ራሱን መከላከል ይችላል። የጠላት ራዳርን ማፈን ይችላል። የሚሳዔል ጥቃት ቢሰነዘርበት ፍንዳታ የማያስከትል ከፍተኛ ብርሃንና ሙቀት ያለው ጨረር በመልቀቅ የተቃጣውን የሚሳዔል ጥቃት አቅጣጫ ያስቀይራል።
‘ኤር ፎርስ ዋን’ አየር ላይ ሳለ ነዳጅ መሙላት ይችላል። አውሮፕላኑ ላይ የተገጠሙት የመገናኛ ቁሳቁሶች ፕሬዝደንቱ በየትኛውም የዓለም ክፍል ላይ ትዕዛዝ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።
በአውሮፕላኑ የፕሬዝዳንቱ መቀመጫ የሚገኘው በፊተኛው የአውሮፕላኑ ክፍል ሲሆን የጋዜጠኞች መገኛ ደግሞ በአውሮፕላኑ የመጨረሻ ክፍል ነው።