April 1, 2024 – Zemedkun Bekele
ይሄም አስቸኳይ ነው
ለአዲስ አበባ ዐማሮች…!
“…ዛሬም በድጋሚ ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ፋኖዎች ይገኙበታል ተብሎ በሚታሰብትና፣ የጦር መሳሪያ ይኖራቸዋል ተብለው የሚገመቱ የዐማራ ተወላጆች ቤት ላይ በድጋሚ ኦፕሬሽን ይሠራል ብለዋል።
“…ዛሬ ሌሊትም የአዲስ አበባ ዐማሮች ቤት በኦሮሙማው አራዊት ይበረበራል። ወርቅ፣ የከበረ ማዕድን፣ የውጭ ሀገር ገንዘብም ከተገኘ ይዘረፋል። ውድ ውድ ሞባይልም ይነጠቃል።
• ሁለት ማሳሰቢያ…
፩ኛ፦ ፋኖ ነን፣ የሚሸጥ መሣሪያ አለን ግዙን የሚሉ ደላሎች ሥልጠና ተሰጥቷቸው አዲስ አበባ ተሰማርተዋል። አገኘሁ ብላችሁ ለመግዛት ምልክት ካሳያችሁ በሕይወት እንደማትመለሱ ዕወቁ። ከማታውቁት ሰው ጋር ከማውራት ተቆጠቡ።
፪ኛ፦ የወደቀው የአቢይ አህመድ አገዛዝ ከተማ ጳጳሳትን፣ ፓስተሮችን፣ ሼኮችን፣ ባለሀብቶችን፣ ሴቶችን ሰብስቦ እንደወተወተው ሁሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሊስትሮዎችን እና ወያሎችን በመሰብሰብ ተሳፋሪም ሆነ ጫማ የሚያስጠርግ ሰው ስለ ፋኖ የሚያወራ ካያችሁ ጠቁማችሁ አስይዙ፣ ይህን ባታደርጉ እኛው እንሰልላችሁና ከከተማው እናስወግዳችኋለን መባላቸው ተሰምቷል። ጎበዝ ሊስትሮ ፊት ጮጋ በሉ ተብላችኋል።
• ዐማሮች ሰምታችኋል…!