April 1, 2024 – Konjit Sitotaw
ኢሠማኮ፣ መንግሥት የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይደራጁ የሚከለክለውን ሕግ እንዲያሻሽል መጠየቁን ሸገር ዘግቧል።
በኢትዮጵያ አሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች እንዳይደራጁ መከልከላቸው በኅብረት መብታቸውን ለማስከበር እንዳይችሉ አድርጓል ሲሉ የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ኢሠማኮ በመንግሥት ሠራተኞች ላይ በሚደርሰው የመብት ጥሰት ዙሪያ መከራከር እንዳልቻለም ካሳሁን ገልጸዋል ተብሏል።
ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅትን የመንግሥት ሠራተኞችን የመደራጀት መብት የሚፈቅደውን ሕግ ያጸደቀች ቢኾንም፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጁ የመደራጀት መብት ያላቸው ግን የግልና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሠራተኞች ብቻ ናቸው።