April 3, 2024 – Konjit Sitotaw
ሳውዲ አረቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ህግ ተላልፈዋል ያለቻቸውን ከ500 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሰረች
ሳውዲ አረቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ ለመግባት ሞክረው ህግ ተላልፈዋል ያላቻቸውን 966 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ባለስልጣናቱ አስታወቁ።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ 59 በመቶ ወይም 569 ገደማ የሚሆኑት ዜጎች ኢትዮጵያዊውያን ናቸው ተብሏል። ሀገሪቱ በአጠቃላይ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ባደረገችው የተቀናጀ ኦፕሬሽን 21,537 ሰዎችን ማሰሯ ተነግሯል።
በሀገሪቱ የድንበር ህግን የጣሱ፣ የሌላ ሀገር ዜጎችን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ የረዱ እና ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የሌላ ሀገር ዜጎች እስከ 15 አመት የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል መባሉን አረብ ኒውስ ዘግቧል።