April 3, 2024 – Konjit Sitotaw
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ብልፅግና ፓርቲ በፕሪቶሪያ ውል መሰረት ፓለቲካዊ ውይይት ለመጀመር መስማማታቸው ተገለጸ።
ህወሓት በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፁ ባሰራጨው መረጃ ፥ በብልፅግና ምክትል ፕረዚደንት አቶ አደም ፋራህ የሚመራ ቡድን ዛሬ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም በመቐለ ከህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር ተወያይቷል።
የሁለቱም ፓለቲካዊ ፓርቲዎች የፓለቲካ ውይይት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ቀደም ብሎ መጀመር እንደነበረበት በመተማመን በአጭር ጊዜ ውስጥ ውይይት እንዲጀምሩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ህወሓት ገልጿል።