April 3, 2024

የብልጽግና ፓርቲ 14 ሚልየን አባላት በሥራ ወይስ በአበል?

 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባቀረቡት የሦስት ቀናት የፕሮጀቶች ጉብኝት፣ የውይይት እና የስልጠና መርሃ ግብር መሰረት ለውይይት ተቀምጠው ነበር።

በውይይቱ የተነሱ ሃሳቦችን የተተቸው እና የተሞገሰው ውይይቱ፣ የፖለቲካ ምህዳር ስለመጥበቡ፣ የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ሃብትን አጠቃቀም እና ሠላም በሚሉ ጉዳዮች ተመልክታዋለች።

የፖለቲከኞች እስር፣ የብልጽግና የህዝብ ሀብት መጠቀምና የሌሎች ፓርቲዎች መቀጨጭ፣ የፓርቲዎች ብዛት ከ5 ባይበልጥ መባሉ 

https://addismaleda.com/archives/36399

By  Ilyas Kifle

 –

03/04/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባቀረቡት የሦስት ቀናት የፕሮጀቶች ጉብኝት፣ የውይይት እና የስልጠና መርሃ ግብር መሰረት ለውይይት ተቀምጠው ነበር። 

የተተቸው እና የተሞገሰው ውይይቱ

የውይይት ጥሪው ፋይዳ ቢስ እና ከቴአትርነት ያለፈ አይደለም በማለት 15 የሚጠጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጥሪውን ውድቅ በማድረግ የኮነኑት ቢሆንም ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ በርካታ የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች ተገኝተው ሃሳብ አቅርበዋል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ስብሰባው የ“ማደናገር እና ማሳመን” የፖለቲካ “ስልታቸው” አካል ነው ብሏል።  

“የብልፅግና ፓርቲ መሪ እና የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ ስልጣን አዉራሻቸዉ እና እንደ አሳዳጊያቸዉ እንደ ህወሃት ከወር በላይ ለሚሆን ጊዜ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ አካላት ጋር ውይይት አደረጉ በሚል ርእስ፣ ምንም ለዉጥ የማያመጣ የገጽታ ግንባታ ስብሰባ እያደረጉ ነው” ሲልም ባልደራስ ተችቷል። 

13 አካባቢ የሚደርሱ አባላት ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ኮከስ የውይይት ጥሪውን ውድቅ ማድረጉ አይዘነጋም። አዲስ ማለዳ ከውይይቱ እንደተመለከተችው ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት አድርገው እንደነበረ ገልጸው መሳካቱን አድንቀዋል። 

የፖለቲካ ምህዳር ስለመጥበቡ 


ተጨማሪ ጽሑፎች:


የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እየጠበበ ስለመሆኑ፣ ለመንግስት ልጅ እና የእንጀራ ልጅ የሆኑ ተፎካካሪ ድርጅቶች መኖር፣ በተመጣጣኝ አውድ ውስጥ ፉክክር እንዳይደረግ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ሃብትን መጠቀም የወቅቱ አንገብጋቢ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መሆናቸው ተነስቷል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ አይታይበትም ብለው እንደማንኛውም ውድድር በሕግ የተገደበ እንጂ የጠበበ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል። ይልቁንም ለፖለቲካ ፓርቲዎች መዳከም መንስዔው ብዛታቸ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዚህ ጥያቄያቸው ግን በፖለቲከኞች እና በፓርቲዎች ላይ የሚደርስ መዋከብ እና ከሕግ ውጪ የሆኑ እስሮችን በመጥቀስ ነበር። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በውይይቱ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ብዛት መቀነስ እንዳለበት ገልጸው “ብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ አምስት፣ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች” ካሉ ለንግግርም ለመደጋገፍም አመቺ ይሆናል በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ሃብትን አጠቃቀም

በዚህ ሳምንት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ ያገኙት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በጅቡቲ በተደረገ ዝግጅት ላይ ፓርቲያቸው ከ14 ሚልይን በላይ አባላት እንዳሉት መግለጻቸው አነጋጋሪ ነበር። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፓርትያቸው የመንግስትን ሀብትና ንብረት እየተጠቀመ አባላት መመልመሉ አግባብ ነው ወይ ሲል ጠይቋል። 

ዐቢይ አህመድ የመንግስት ስራን በመንግስት ገንዘብ እንደሚፈጽሙ ተናግረው እንደፓርቲ ከሚሰሩ ስራዎች ለይታችሁ እዩ ሲሉ ተናግረዋል። ይኹን እንጂ የተወሰን ብክነት እንደሚኖር እና የመንግስትና ፓርቲ መቀላቀል እንደሚኖር አስረድተው ይስተካከላል ብለዋል። 

በመድረኩ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የግዙፍ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ፍሰት እና አስተዳደር በስርዓት የሚመራ ስለመሆኑ ጠይቆ የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገንዘብ ከግብር ውጭ በሆነ መደበኛ ያልሆነ መንገድ እንደሚሰበሰብ ተናግረው ነገር ግን ገንዘቡ በስርዓት ነው የሚተዳደረው ሲሉ ተናግረዋል። 

ሠላም

የሰላም ጥያቄ በሁሉም በኩል የተነሳ ሲሆን ከታጣቂዎች ጋር የተለየ ስምምነት እንዳልነበረ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ለውጡን ተከትሎ ስልጣን ፈልገው የነበሩ አካላት ስልጣን ስላላገኙ ወደ ትጥቅ ትግል ተመልሰዋል ብለዋል። ይኹን እንጂ የትኛውንም የሰላም አማራጭ መንግስታቸው እንደሚደግፍ እና በቅርቡ በተፎካካሪ ፓርቲው ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ የተጀመረውን የሰላም ሂደት እውቅና ሰጥተዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ለታጠቁ ኃይሎች “የተለየ” የሚቀርብ የድርድር ሃሳብ እንደሌለ ገልጸው በሰላምና በንግግር ፖለቲካዊ ችግሮችን በመፍታት የታጠቁ ወገኖች ደግሞ ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ ማድረግ ነው። ኢዜማ በመድረኩ ላይ የአካባቢያቸውን ሰላም ማስጠበቅ ያልቻሉ አስተዳዳሪዎች እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል።

በተጨማሪም የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ስራ ላይ የብልጽግና ፓርቲ ተጽዕኖ እያረፈበት መሆኑ የተነሳ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተባብለዋል። ከዚህ ባለፈም ባሕላቂ የግጭት አፈታት ስርዓቶች በህግ ተደግፈው የአገር አቀፍ እና የክልል ህጎች ውስጥ ቢካተት ግጭቶችን በፍጥነት መፍታት እንደሚቻል ሃሳብ ቀርቧል።