ብልጽግና ፓርቲ “ፍሬያማ” ያላቸው 6 ዓመታት ለአገሪቱ አደጋ ናቸው ተባለ
ያለፉት ስድስት ዓመታት መንግስት ቅድሚያ መስጠት ላለበት ጉዳይ ትኩረት ሳይሰጥ እና አገሪቱን የመበተን አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራት ተስፋፍተው ያሉበት እንደሆነ ከአዲስ ማለዳ ጋር ቆይታ ያደረጉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ገለጹ።
የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ስድስተኛ ዓመት መጋቢት 24 ቀን 2016 ነበር። በተለያዩ አካባቢዎች የድጋፍ ሰልፎች ከመደረጋቸው ጎን ለጎን የፓርቲው አባላት “ፍሬያማ” ስድስት ዓመታት እንዳለፉ እየገለጹ ነው።
ብልጽግና ፓርቲ የትኛውም ምድራዊ ኃይል የማያደናቅፈው የለውጥ ጉዞ ላይ ነን ቢልም ተፎካካሪዎቹ አገሪቱን የሚበትን አደጋ መንሰራፋት፣ ለዜጎች ሰላም ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከጎረቤት አገራት ጋር መቃቃር እና… https://addismaleda.com/archives/36407