Mengistu Musie

  · YouTube  · 

ኢሓፓን የመሰረቱት እና በመጀመሪያው አመታት በጸሐፊነት የመሩት ቀደምት ሁለት አብዮታውያን ብርሐነመስቀል እረዳ እና ዶ/ር ተስፋየ ደበሳይ ናቸው። ብርሐነ መስቀል እረዳ የመጀመሪያው የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሲሆን የኢሕአፓን ጠንሳሽ ጦር (ኢሕአሰን) አሲምባ ይዞ የገባ የሰራዊቱም መስራች እንደሆነ ሁሉ። ብርሐነ ለ1966 አብዮት ምክንያት ለሆነው የኢትዮጵያ ተማሪወች እንቅስቃሴ ቀደምት የንቅናቄው መሪወች ውስጥ አንዱ እና ልክ የለሽ ቀደምት አብዮታዊ እና ከመሰረተው ድርጅት ጋር በልዩነት እስከተለያየ ድረስ ብዙ አብዮታውያንን ወደ ኢሕአፓ ያስገባ እና ያደራጀት/ያታገለ ታጋይ ነበር።

ከብርሐነ መስቀል ቀጥሎ ዶ/ር ተስፋየ ደበሳይ የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ሆኖ በ ነሐሴ 1967 አዲስ አበባ በተካሄደው እና የመጀመሪያ የፓርቲው ኮንግረስ በሆነው ስብሰባ ተመርጧል። ዶ/ር ተስፋየ ደበሳይ መስዋእት እስከሆነበት ቀንም ድርጅቱን በጸሐፊነት መርቷል።

ከላይ የጠቀሥኋቸው ሁለቱም የኢሕአፓ መሪወች ለሰማይ ለመሬት የከበዱ ምሁራን እና ቀደምት አብዮታውያን ነበሩ። ሁለቱም በሁለት አመታት ልዩነት ተሰውተዋል። ጓድ ተስፋየ እጅ ላለመስጠት እራሱን ከሰባተኛ ፎቅ በመወርወር ለጠላቶቹ ቁርጠኝነትን በንቀት አሳየ። ለተከታይ ጓዶቹ ፍጹም አላማን እስከህይወት መስጠትን አስተምሮ አለፈ። ቀዩ ሽብር በተካሄደበት በዚያ ሁለት ተከታታይ አመታት የኢሕአፓ አባላት ጀግንነት — ፍጹም ወደር የለሽ እንደነበረ ሁሉ ጠበንጃ የያዘን አፋኝ ብርክ ያስያዘ የትውልድ ገድል አሳይቶ አልፏል።

የዛሬዋ ደስታ ጥላሁን የዚህ አንጋፋ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ስትሆን የዩኒቨርስቲም መምህር ናት። ከዚህች ትንታግ ታጋይ ይህ ቃል ይወጣል ብሎ ያልጠበቀው አብይ አህመድ ሴትነቷ ምሁርነቷን እና ችሎታዋን ሸፈነበት በንቀት የጠበቀው ጥያቄወቿ ሁለት ሰአታት አረፋ ያስዳፈቀችው። ወጣቷ ምሁር እና የኢሕአፓ ዋና ጸሐፊ ደስታ ጥላሁን የዘመናችን የዚህ ታጋይ ድርጅት እና የእነዚያ ቀደምት አብዮታውያን ሰማ’እታት ተኪ መሆኗ ሌላ የታሪክ ገጠመኝ ሳይሆን ኢሕአፓዊነት ጀግንነት እና ስለሕዝብ እና ሐገር መስዋ’እትነትን በጀግንነት መወጣት ነው። አዎ ፋኖ ተሰማራ፤ ፋኖ ተሰማራ እንደሆችሚንህ፤ እንደቸጉቬራ!!!

HAMER MEDIA | ‹‹ማን እንደላከሽ አውቃለሁ›› ዶ/ር ዐቢይ የሰጡት አስደንጋጭ መለስወጣቷ ፖለቲከኛ ዶ/ር ዐቢይን ስታፋጥጣቸው የተፈጠረው ጉድ

YOUTUBE.COM