April 14, 2024 – Konjit Sitotaw
በትግራይ ክልል መኾኒ ወረዳ መኾኒ ከተማ የሚገኙ የጦርነት ተፈናቃዮች ዛሬ ጧት የተለያዩ ጥያቄዎችን በማስተጋባት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ሰልፈኞቹ፣ የትግራይ እና አማራ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው አላማጣ እና ራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ፣ ከመኾኒ ወደ ኩኩፍቱ ከተማ እና በሪ ተክላይ ባካሄዱት ሰልፍ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከአላማጣና ራያ አካባቢዎች እንዲወጡና ወደ ቀያቸው ባስቸኳይ እንዲመለሱ መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
በሪ ተክላይ አካባቢ የሠፈረው የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች፣ ለሰልፈኞቹ ንግግር አድርገዋል ተብሏል።