የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር፣ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር “ፈጽሞ ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል” ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጧል።
መግለጫው፣ ባኹኑ ወቅት በኹለቱ አገሮች መካከል መካከል ያለው ድንበር፣ በዓለማቀፉ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት “ባግባቡ የሚታወቅ እና በሕግ የተረጋገጠ ድንበር” መኾኑን ጠቅሷል።
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ወይም በኤርትራ እና ትግራይ ሕዝቦች መካከል የሕግ ጥሰት ካልኾነ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ግጭት የሚያስነሳ ጉዳይ እንደሌለ በመግለጫዋ የጠቀሰችው ኤርትራ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከፍተኛ ውድመት ካስከተለው የኹለቱ አገሮች የድንበር ጦርነት ትልቅ ትምህርት ወስዷል ብላለች።