
ከ 7 ሰአት በፊት
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ኢራን እስራኤል ላይ የጥቃት እርምጃ ከወሰደች በኋላ ከትናንት ሰኞ ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል።
የዓለም የነዳጅ ዋጋ ማነጻጸሪያ የሆነው የድፍድፍ ነደጅ ዋጋ እያሽቆለቆለ ሲሆን በበርሜል ወደ 90 ዶላር እየተጠጋ ይገኛል።
ተንታኞች ኢራን እስራኤል ላይ ያደረሰችው ጥቃት ዓለም አቀፍ የገበያ ሰንሰለት ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ወደፊት የሚታይ ይሆናል ብለዋል
የዓለም የነዳጅ ዋጋ መለዋወጥ በርካታ ሀገራት ለምርት የሚመረኮዟቸውን የቤንዚል እና ናፍጣ ዋጋን ተቀያያሪ በማድረግ የዓለም ገበያ እንዳይረጋጋ ያደርጋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዓለም ዙሪያ ለታየው የምርቶች ዋጋ ማሻቀብ ዋነኛው ምክንያት የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ ነው።
በአውሮፓውያኑ 2022 ሩስያ ዩክሬንን ስትወር የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ ወደ 120 ዶላር ጨምሯል። የዚህም ምክንያት ሩስያ ላይ ምዕራባውያን የጣሉት ማዕቀብ ነው።
ይህ እርምጃ የነዳጅ ዋጋ ብቻ ሳይሆን በዓለም የምርቶች ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሬ እንዲታይ ሰበብ ሆኗል።
ታዲያ እስራኤል አሁን የምትሰጠው አጸፋ የዓለም የነዳጅ ዋጋን ለመወሰን ወሳኙ እንደሆነ ታምኗል።
የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ከኢራን ጋር የገባነው ፍጥጫ አላበቃለትም ብለዋል።
ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ኢራን ባለፈው ቅዳሜ እስራኤል ላይ ለፈጸመችው ጥቃት ምላሽ ሲሰጡ ነው።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 92.18 ዶላር የነበረ ሲሆን ይህም ከጥቅምት ወር ወዲህ የተመዘገበው ከፍተኛው ዋጋ ነበር። ሆኖም ትላንት ሰኞ ወደ 89.50 ዶላር ወርዷል።
- ከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞች በሱዳን ኃይሎች እንደምርኮኛ መያዛቸው ተናገረከ 8 ሰአት በፊት
- ጆ ባይደን ከዶናልድ ትራምፕ፡ ለፕሬዝዳንትነት አሸናፊውን የሚለዩ አራት ወሳኝ ነጥቦችከ 8 ሰአት በፊት
- በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ15 ሚያዚያ 2024
ሌላው በዓለም ገበያ አስተማማኙ ኢንቨስትመንት እንደሆነ የሚቆጠረው የወርቅ ዋጋም ቀንሷል።
የወርቅ ገበያ ባለፈው አርብ በወቄት 2 ሺህ 431 የነበረ ሲሆን ይህም ከፍተኛው የወርቅ ዋጋ ሆኖ ተመዝግቧል። አሁን ዋጋው በወቄት ወደ 2 ሺህ 332.9 ዶላር ቀንሷል።
ኢራን የዓለም ሰባተኛዋ ከፍተኛ ነዳጅ አምራች ሀገራት ስትሆን ሶስተኛዋ ትልቁ የነዳጅ ላኪዎች ህብረት ወይም ኦፔክ ሀገራት አምራች ነች።
ታዲያ ተንኞች የዓለም የነዳጅ ዋጋን የሚወስነው በግጭቱ ሆርሙዝ ሰርጥ ምን ያህል ተጽዕኖ ውስጥ ይወድቃል የሚለው እንደሆነ ይናገራሉ። ሆርሙዝ ሰርጥ ነዳጅ የሚመላስበት መስመር ነው።
በኦማን እና ኢራን መካከል ያለው ይህ ሰርጥ የዓለም እስከ 20 በመቶ የሚደርሰው ነዳጅ የሚጓጓዝበት ነው።
የኦፔክ አባላት የሆኑት ሳዑዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ዩኤኢ ኩዌት እና ኢራቅ ይህንን መስመር ተጠቅመው ነዳጅ ይልካሉ።
ባለፈው ቅዳሜ ኢራን በዚህ ሰርጥ ሲተላለፍ የነበረ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያለውን መርከብ ይዛለች።
በሰርጡ ይህንን አይንት ውዝግብ ከቀጠለ እና ጉዞዎች የሚስተጓጎሉ ከሆነ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያናጋው እንደሚችል ተሰግቷል።