
ከ 4 ሰአት በፊት
ከሦስት ዓመት በፊት የዓለም መነጋገሪያ የነበረው እና በአውስትራሊያ ፓርላማ ውስጥ አንዲት ሴት ተደፈረች የሚለው ጉዳይ እውነት ነው ሲል ፍርድ ቤት አረጋገጠ።
ፖለቲከኛው ብሩስ ሌርማን የስራ ባልደረባውን ደፍሯታል የሚለውን ክስ የካደ ሲሆንን ይህንን በተመለከተ ስለጉዳዩ ያናገረውን ኔትዎርክ 10 የተባለ የቴሌቭዥን ጣብያ በስም ማጥፋት ከሷል።
ጣብያው ስህተት አለመሥራቱን ገልጾ የተከራከረ ሲሆን ጉዳዩ ቁጣ መቀስቀሱም የሚታወስ ነው።
ሌርማን ሂጊንስን እንደደፈረ እና “ሆን ብሎ ውሸት” ተናግሯል በማለት ፍርድ ቤት ለጣብያው ወስኗል።
በቃለ መጠይቁ ወቅት እያለቀሰች የነበረችው ሂጊንስ፣ እአአ በ2019 በሚኒስትሩ ቢሮ ውስጥ ባለ ሶፋ ላይ ባልደረባዋ ከላይዋ ሆኖ እየደፈራት እንዴት እንደነቃች በዝርዝር ተናግራለች።
ሌርማን በበኩሉ ካንቤራ ውስጥ ምሽቱን ሲጠጡ አምሽተው በታክሲ ወደ ቢሮ መመለሳቸውን እና በኋላም ሁለቱም ወደሚፈልጉበት አቅጣጫ መሄዳቸውን ተናግረዋል።
የሌርማን የስም ማጥፋት ክስ ውድቅ እንዲደረግ የወሰኑት የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኛው ማይክል ሊ የ28 ዓመቱ ፖለቲከኛ ከሂጊንስ ጋር ‘በማንኛውም’ ሁኔታ ወሲብ ለመፈጸም ፍላጎት እንደነበረው ገልጸዋል።
“ስለዚህ ፍላጎቱን ለማሟሟላት በማሰብ… (ሌርማን) ፈቃደኛ መሆኗን ወይም አለመሆኗን ከግምት ሳያስገባ ወሲብ ግንኙነቱን ቀጠለ” ብለዋል።
የስም ማጥፋት ጉዳዮች ከወንጀል ጉዳዮች አንጻር አነስ ያለ ማስረጃ ይፈልጋሉ። በዚህም ተከሳሹ ጥያቄዎቹ እውነት የመሆን ዕድል ያላቸው መሆናቸውን ብቻ ማረጋገጥ አለበት።
ይህ ውሳኔ ግን ለዓመታት የአገሪቱ መነጋገሪያ የነበረው ጉዳይ የመጀመሪያው የህግ ውሳኔ ነው።
የሂጊንስ የመደፈር ክስ የአገሪቱን የባህል እሴት የነቀነቀ ሲሆን፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት ተቃውሞ እና የፓርላማው ባህል ላይ ጉልህ የሆነ ጥያቄ አስነስቷል።
ሌህርማን በ2022 የወንጀል ክስ ቀርቦበት የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ በዳኞች ስነምግባር ጉድለት ምክንያት ተቋርጧል። በኋላም ለሂጊንስ የአዕምሮ ጤና ሲባል የክስ ሂደቱ በድጋሚ መታየቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
“ሌህርማን ስህተት ሰርቷል” ሲል ዳኛ ሊ በኔትወርክ 10 እና በዝግጅት አቅራቢዋ ሊሳ ዊልኪንሰን ላይ በቀረበው የስም ማጥፋት ክስ ዙሪያ ውሳኔያቸውን አሰምተዋል።
በወቅቱ አገሪቱን ሲያስተዳደር በየነበረው የሊበራል ፓርቲ ውስጥ የነበሩ የሂጊንስ አለቆች ጉዳዩን ለማድበስበስ ወይም ሂጊንስ ላይ ጫና ለማድረግ ሞክረዋል የሚለው ክስ “ከእውነታነት ይልቅ በግምት ላይ ተመሠረተ ነው” ብለዋል።
ሆኖም በመድፈር ክስ ዙሪያ ያሉት ማስረጃዎች “እውነትነት” እንዳላቸው ወስነዋል።

በአጠቃላይ ግን ጉዳዩ “በርካታ ውጥንቅጦች የሚያስከትል ነው” ሲሉ ዳኛ ሊ ተናግረዋል።
በስም ማጥፋት ጉዳዮች ላይ ዳኞች በምስክሮች ታማኝነት ወይም ባህሪ ላይ ፍርድ ለመስጠት እንዲረዷቸው ብዙ ጊዜ ተጨባጭ የሚመስሉ ማስረጃዎችን ይፈቅዳሉ።
ችሎቱ ከአምስት ሳምንታት በላይ አንዳንድ ጊዜ አስገራሚ ማስረጃዎችን የሰጡትን ጨምሮ ከ12 በላይ ምስክሮች ሰምቷል።
ፍርድ ቤቱ ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡ የከንፈር አንባቢ፤ ከሂጊንስ ወላጆች ምስክርነት እና በፓርላማ ውስጥ ያሉ የሁለቱም ባልደረቦች የሰጡትን ምስክርነት ሰምቷል።
ሌላኛው የቴሌቭዥን ጣብያ ሰቭን በበኩሉ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እንደ እጅ መንሻ ለወሲብ እና ለአደንዛዥ እጾች ከፍሏል የሚሉ አቤቱታዎችን ለመስማትም በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ላይ ክሱ ተከፍቶ ነበር።
ሰቭን ክሶቹን ውድቅ ቢያደርግም ሰኞ ዕለት የስፖትላይት ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ባለደረቦቹ ጥYaቄ ውስጥ በመመውደቃቸው ጣብያውን መልቀቁ ታውቋል።
ዊልኪንሰን “ዛሬ ለአውስትራሊያዊያን ሴቶች ደስተኛ ነኝ” ስትል ከፍርድ ቤቱ ውጭ ሆና ገልጻለች።
የኔትዎርክ ቴን በበኩሉ የዳና ሊ ውሳኔ “በአገሪቱ ውስጥ ላሉ ለሴቶች ድምጽ ለመሆን ለደፈረችው ብሪታኒ ሂጊንስ ትክክለኛ ነው” ሲል መግለጫ አውጥቷል።
“ውሳኔው እውነት ማሸነፉን አሳይቷል።”
ከፍርድ ቤት ሲወጣ ምንም ያልተናገረው ሌርማን፣ አሁን በሁለቱም ወገኖች ለተጠራቀመ በሚሊዮኖች ለሚቆጠር ህጋዊ ወጪዎች ተጠያቂ ይሆናል። ትክክለኛው የገንዘብ መጠን በቀጣይ የሚሰላ ይሆናል።