ነዐመን ዘለቀ ፡ በፕሪቶሪያ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት ትጥቅ ሳይፈታ እንዲቀመጥ አብይ አህመድ ሆን ብሎ የተተወው ህወሃት በወታደራዊ ሃይል፣ በከባድ መሳሪያዎች ጭምር ፣ የራያ ዋና ከተማ የሆነችውን አላማጣን መቆጣጠሩን ልዩ ልዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ይህ ሲሆን ደግሞ በአካባቢው የነበረው የመከላከያ ስራዊት ዝም ብሎ ሲያይ እንደነበር፣ ምንም አይነት የመከላከል እንቅስቃሴ እንዳላደረገ የአላማጣ የብልጽግና ሃላፊዎች ለዜና አውታሮች በሰጡት ቃል ምልልስ ተናግረዋል። “የፌደራል መንግስት የራያን ህዝብ ከድቶታል” ነው ያሉት የብልጽግና የራያ ሃላፊዎች፣ ሁለት ቀን የፈጀ ፣ መከላከል በኋላ ከአፈገፈጉበት አካባቢ በስልክ በሰጠው ቃል ምልልስ።
የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ (ህወሃት) መሪዎች (በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ) ካለፉት ውድቀቶችና ክሽፈቶቻቸው መቼም የማይማሩ መሆናቸውን እያሳዩ ነው፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አይተኬ ህይወት የቀጠፈ አስከፊ ጦርነት፣ ይህ ነው የማይባል ውድመት፣ የፓለቲካና የስብእና ውድቀትና ውርደት አስተምሮ አልተወሰደም። አሁንም እንደትላትናው የተስፋፊነት ፍላጎታቸውን/ግባቸውን ለማሳካት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ አ በወታደራዊ በሃይል ይዘዋል። ይህን ዳግም ጥፋት መንገድ በመከተል በተዘጋጀላቸው ወጥመድ ዘው ብለው ገብተዋል። የአማራን ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር የማያባራ ግጭት ውስጥ የሚከት የጥፋት እርምጃ በመውሰድ በከፍተኛ ውጥረትና ስጋት ውስጥ የሚገነው ፋሽስታዊው የበሻሻ ደላላ የአብይ አህመድ የዘወትር ጸሎት እንዲሰምርለት አድርገዋል። በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ህወሃት ትጥቅ ሳይፈታ “ፍቶአል፣ እየፈታ ነው፣ ህወሃት ዳግም ጦርነት አይሞክርም፣ የአማራ ህዝብ የደህነት ስጋትም የለበትም፣” ሲሉ የአብይ አህመድ ካድሬዎች ፣ ሬድዋን ሁሴን ጭምሮ ህዝብን ሲያጭበረብሩ እንደነበር አይዘነጋም። አብይ አህመድና የብልጽግና ካድሬዎቹ መርህ አልባ፣ የማጭበርበር፣ የክህደት መንገድ ኢትዮጵያን ከአንድ እልቂትና ውድቀት ወደ ሌላ እልቂትና ውድቀት፣ ውድመት መንገድ እየገፋ፣ ህዝብንም ለማያባራ መከራ እየዳረገ ቀጥሎአል ። አስመሳዩ ከሃዲ አብይ አህመድ ከህወሃት ጋር የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ከህወሃት ጋር በተፈራረመ ማግስት የአማራ ልዩ ሃይልን፣ እንዲሁም ፋኖን ትጥቅ አስፈታለው በማለት ውሳኔ ማድረጉ የሚያወስ ነው። “የአማራ ህዝብ የደህንነት ስጋት ከህወሃትም ፣ ከኦነግ ሸኔ ይመነጫል፣ ህወሃት ትጥቅ ሳይፈታ ፣ ኦነግ ሸኔ ፣ አማራ ክልል ድረስ በመዝለቅ ብዙ ጥፋትና ውድመት እያደረሰ ነው፣ የደህንነት ዋስትና ሳናገኝ ትጥቅ መፍታት ለአደጋ ያጋልጠናል፣ ወዘተ “ በማለት ጥያቄ ባነሳው የአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ይህ ነው የማይባል ውድመትና የንጹሃን እልቂት እያደረሰ እስካሁኑ ሰአት ቀጥሎአል። ቀደም ብሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን “የፕሪቶሪያው ስምምነት ይከበር፣ የፌደራል መንግስት የሚያደርገው ሁሉ ታክቲካል ስሌትና የብልጠት አካሄድ መሆን የለበትም፣ የሰላም ስምምነቱ በመርህ ይሁን በማለት ብዙዎች ሲጠይቁ፣ ሲጽፉ ፣ተማጽኖ ሲያቀርቡ አሻፈረኝ ብሎ “የትግራይን ጥርስ አውልቀናል፣ የአማራው ይቀረናል” በሚል እብሪት በተወጠሩ የኦሮሚያ ብልጽግና መሪዎች ግፊት ግፊት ጭምር የአማራን ህዝብ/ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የቆረጠው አብይ አህመድ ያለ የሌለ የጦር ሃይሉን የክልሉ ህዝብ ላይ አዘመተ። የነበረው እንዳልነበረ ሆነና፣ የኦሮሞያ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች ከህወሃት መሪዎች ጋር ሽር ጉድ ሲሉ፣ በአንድ እንትን እንትን እናድርግ እስኪመስል፣ “የሞተ ተጎዳ” እያለ ከንፈሩን በቁጭት የሚመጠውን የኢትዮጵያን ህዝብ ስንት ጉድ አሳዩት።
የአብይ አህመድና የሽመልስ አብዲሳ ተወካዮች፣ የኦሮሚያ ብልጽግና መሪ ካድሬዎች መቀሌ ድረስ በመጓዝ፣ በአሸንዳ በአል ላይ በአደባባይ በአማራ ህዝብ ላይ በጋራ ለመተባበር ፣ በአደባባይ እስከማወጅም ደረሱ። በሚሊዮኖች ኢትዪጵያውያን ሞትና በቢልዪኖች ዶላር የሚገመት የህዝብ ንብረት ውድመት ተጠያቂ የሆኑትን የህወሃት መሪዎች በሰላም ስምምነት ስም ፣ በመስቀል አደባባይ ድግስ ደግሶ፣ ሸልሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ቁስል ላይ ጨው ነሰነሰ፣ ያልደረቀው የህዝብ ቁስል ላይ እንጨት ሰደደበት። ሀገሬ ብለው፣ ቤት፣ ንብረቱን፣ ቤተስቡን ትቶ ኢትዮያን ለመታደግ፣ በየዱር ገደሉ ሲፋለሙ የተሰዉት መቶ ሺዎች ኢትዮጵያውያን ደም ሳይደርቅ፣ በግፍ የተጨፈጨፈው የአማራ ህዝብ፣ የአፋር ህዝብ ከደረሰበት መጠነ ሰፊ የህይወትና የንብረት ውድመት ስያገግም፣ ሚስቶች የባሏን ፣ እናቶች የልጆቿን፣ መሪር ሃዘን እውጥተው ሳይጨርሱ ይህን መሰለ ክህደትና የብሂራዊ ነውር በነውረኛው ካሃዲ አብይ አህመድ ተፈጸመ። የውጤቱን የመጀመሪያ ምእራፍ አሁን እያየነው ነው። አብይ አህመድ አርቆ ማየትም ፣ ማሰብም አይችልም። ምርቃናውን እና ቅዥቶቹን ከማርካት በዘለለ ስትራቴጂካዊ እስተሳሰብ ጋር እይተዋወቅም።
መርህም ፣ እሴቶችም እልፈጠረበትም። ከማስመሰል ውጭ። ሁሉን አዋቂው፣ ሁሉን አድራጊው ፣ የ7ኛ ንጉስ ገድብ የለሽ የስልጣን ፍላጎቱን ለማርካት ማለቂያ የሌላቸው የሸፍጥና የክህደት ዘይቤዎች በመጠቀም በኢትዮጵያ ህዝብ ደም፣ ህይወትና፣ እምባ ኪሳራ ስልጣኑን ለማስቀጠል የቆረጠ ፋሽስታዊ ነው ስንል በምክነያት ነው’ ።የአብይ አህመድና የኦሮሚያ ብልጽግና ጋጠ ወጦችና ስግብግቦች የክህደትና የሸፍጥ እርምጃዎች ዳግም ለተቀሰቀሰው ጦርነት፣ ለሚደርሰውም ጥፋት፣ ውድመትና፣ እልቂት ከህወሃት እኩል ተጠያቂ መሆናቸው የማቀር ነው። https://youtube.com/watch?v=sJMhrOGaTZEAnchor
Breaking የህወሀት ጦር አለማጣ እየገባ ነው፤ ነዋሪው በመሰደድ ላይ ነው፥ የአላማጣ አስተዳደር ከተማዋን ለቆ ወጥቷል። ነዓመን ዘለቀ