Mengistu Musie

የአብይ፤የአማራ እና የትግራይ ባንዳወች

——————————

የአብይ እና የተወሰኑ የህወሓት አጀንዳ አስቀያሪ የወረራ አጀንዳ በአብይ ቤተመንግስት እና በህወሓት አንጃ ቡድን ተሰልቶ እና ታስቦበት የተሰራ አዲስ ስልት ነው። በአላማጣ በኩል እየተንቀሳቀሰ ያለው የጦረኛ አካሄድ እንደሚያሳየው አብይ አህመድን እና የአብይን ጦር ጀነራሎች የወጠረውን የፋኖ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አቅጣጫ የማስቀየር እና ሰርጆ ለመጣል የተዘየደ የአብይ ህወሓት ስልታዊ የጦር እቅድ ነው።

ፋኖ በአብይ አህመድ ጦር ላይ የሳለውን የትግል አቅጣጫ ለማስቀየር የተዘየደው የነዚህ የሁለት ጠባብ ኃይሎች እቅድ ማክሸፍ የሚቻለው የተጀመረውን ትግል በማጧጧፍ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ሊሆን ይገባል። አብይ እና ጠባብ የዘረኛ ቡድኖች በእርግጥም እስትራቴጅአዊ የሶሻል ፖለቲካ ግባቸው አንድ እና ተመሳሳይ ቢሆንም ዛሬ ህወሓት ይህን በአላማጣ የጀመረችው ወረራ ከአላት ወታደራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማይሄድ በመሆኑ አሁንም የፋኖ ትኩረት ለአፍታ ከዋና ደመኛ ጠላት ከአብይ አህመድ ወራሪ ጦር የተለየ አቅጣጫም ሆነ አስተሳሰብ እንዳይኖር ይገባል።

ይህ ስልት እንደምናየው ዛሬ በአማራ ክልል ያለው የባንዳ ቡድን፤ ትግራይ ውስጥ ካለው ባንዳ የተለየ እንዳልሆነ ሁሉ ሁለቱም የባንዳ ቡድኖች (የትግራይ እና የአማራ ባንዳወች) የአብይ አህመድን ትእዛዝ እና እርሱ የሚለውን ፈጻሚ ታዛዦች ስለሆኑ የፋኖ እና የፋኖ ደጋፊ ኃይሎች ለአፍታ ከአብይ አህመድ አይናችሁን እንዳታነሱ መሆን ይኖርበታል!!