ፍሬከናፍር
‹‹ኮሎኔል አስማማው ቀለሙ አገርን ከምንም ነገር አስቀድመው፣ ያካበቱትን ያላቸውን ሁሉ መስጠትና ማገልገል…

በጋዜጣዉ ሪፓርተር

ቀን: April 17, 2024

የመረጃና ደኅንነት ታላቁ ባለሙያን ኮሎኔል አስማማው ቀለሙ (ዶ/ር) ዜና ዕረፍት ተከትሎ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም ካወጣው መግለጫ የተወሰደ፡፡ በሦስቱ የኢትዮጵያ መንግሥታት ለስድስት አሠርታት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሰጡት ኮሎኔል አስማማው፣ ለሙያቸው የተሰጡና በዚህም ለኢትዮጵያ ታላቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ያስታወሰው ተቋሙ፣ ከልጅነት እስከ እስር ቤት የዘለቀ አዲስ ነገር ለመማር፣ ለመፍጠርና ቁልፍ ተግባሮችን ለመሥራት በጥናትና ሙከራ ላይ የተመሠረተ መጋፈጥና በግል ተነሳሽነት ታላላቅ ሐሳቦችን መጀመርና ለፍሬ ማብቃት ዓይነተኛ መለያቸው ነበር ብሏል፡፡