April 20, 2024 – Konjit Sitotaw

የዓለም ጤና ድርጅት “ጆንሰን ኤንድ ጄንሰን” በተባለው የሕጻናት ሲረፕ መድኃኒት ላይ የጤና ማስጠንቀቂያ ሊያወጣ እንደሚችል መናገሩን ሮይተርስ ዘግቧል።

ድርጅቱ ይህን የገለጠው፣ ናይጀሪያ “ቤኒሊን” በተሰኘው የ”ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን” የሲረፕ ዓይነት ላይ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን አግኝቼበታለኹ በማለት ባለፈው ሳምንት ክትባቱን ማገዷን ተከትሎ ነው።

መርዛማው ንጥረ ነገር፣ በጋምቢያ፣ ካሚሮን፣ ኢንዶኔዥያና ኡዝቤኪስታን ከዓመት በፊት ለ300 ሕጻናት ሞት ምክንያት እንደኾነ ዘገባው አስታውሷል።

መርዛማ ንጥረ ነገር የተገኘበት ሲረፕ፣ “ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን” ኩባንያ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ያመረተው ነው።